ቱ. ማ. ኢ ሚያዚያ 22/2015ዓ.ም ቱሪዝም ማሰልጠኛ ኢንስቲትዩት የተቀበለውን ሀገራዊ ተልዕኮ ተቀብለው ላሳኩት አሰልጣኞችና ሰራተኞች ምስጋና ቀረበላቸው ።
በዚህ ፕሮግራም የተገኙት የተቋሙ ዋና ዳይሬክተር የተከበሩ አቶ ጌታቸው ነጋሽ እንደገለፁት ፕሮግራሙን ስንቀበል የከበደን ቢሆንም ጠንካራ አሰልጣኞችና ሰራተኞች በመኖራቸው ስልጠናውን ከዕቅዳችን 90 በመቶ ማሳካት ችለናል፡፡
ይህንን ፕሮግራም እንዲያስተባብሩ ሃላፊነት የተሰጣቸው አንጋፋው አሰልጣኝ አቶ ታደሰ ሞላ ሥልጠናውን በብቃት በመምራት አኩርተውናል ለዚህም ከፍተኛ ምስጋና እናቀርባለን ብለዋል።
አቶ ጌታቸው አክለውም ስልጠናው የሚያስፈልገውን አስፈላጊ ግብዓት በብዙ ጥረት በሟሟላት የተሳተፋችሁ ሁሉ ምስጋና ይገባችኋል ብለዋል፡፡
የፕሮግራሙ አስተባባሪ አቶ ታደሰ ሞላ በስልጠናው ወቅት የነበሩ ጠንካራ ጎኖች፣ ያጋጠሙ ችግሮች ችግሮቹን ለማለፍ የተደረጉ ጥረቶች፣ በሰነድ አቅርበው ውይይት ተደርጎበታል።
በየሙያ መስኩ የተዘጋጁ ሞጁሎችን እደየሙያቸው የተመደቡ አሰልጣኞችም ስራተኞች በባለቤትነት መስራታቸው ይህ ደግሞ ተቋሙ ሌሎች ተልዕኮዎች ቢቀበልም በቀላሉ ማሳካት እንደሚችል ያሳየ መሆኑን አቶ ታደሰ አንስተዋል፡፡
እንደ ሥራው አልጋ በአልጋ ባይሆንም የነበሩ ችግሮችን ለማለፍ የነበሩ ጥረቶችን አመስግነዋል፡፡
በቀረበው ሰነድ ላይ በመወያየት ሁሉም ተሳታፊ ቀጣይ መሻሻል ያለባቸውን ሀሳቦች አንስቶ ከሚመለከታቸው ኃላፊዎች ምላሽ ተሰጥቷል።
የሰራን ሰው ማመስገን እና ዕውቅና መስጠት በሌሎች ሥራዎችም ሊቀጥል እንደሚገባ ከተሳታፊዎች ሃሳብ ተሰጥቷል።

Recent Comments