የካቲት 29/2014ዓ.ም የሥራና ክህሎት ሚኒስቴር፣ቱሪዝም ማሰልጠኛ ኢንስቲትዩት እና የቴክኒክና ሙያ ኢንስቲትዩት በጋራ በመተባበር
በሀገር አቀፍ ደረጃ ለሚዘጋጀው የቴክና ሙያ ስርዓት ትምህርት በቱሪዝምና የሆቴል ዘርፍን የዘርፉን ባለሞያዎች በመጠቀም የቱሪዝም ማሰልጠኛ ኢንስቲትዩት አዘጋጀ።
የስርዓተ ትምህርት ዝግጅቱ ቀድሞ በየተቋማቱ በተበታተነ መልኩ ሲሰራበት የነበረ ወጥነት በማስቀረት እንደ ሀገር የዘርፉን ብቁ ባለሞያዎች ለማፍራት የሚያስችል ዝግጅት እንደሆነ የተቋማችን አካዳሚክ እና ምርምር ዲን ገልጸዋል።
በዚህ ሥርዓተ ትምህርት ዝግጅት የአስጎብኝ ድርጅቶች ማህበራት ፤ የሆቴል ባለሙያዎች ማህበራትና ከተቋማችን እና ከሀገሪቱ የተለያዩ ማሰልጠኛዎች የተውጣጡ የዘርፉ መምህራን ተሳትፈዋል።
Recent Comments