ቱ. ማ. ኢ ሚያዝያ 8/2017 ዓ ም ቱሪዝም ማሰልጠኛ ኢንስቲትዩት አመራርና ሠራተኞች በ2017 ዓ. ም ሀገራዊ የዘጠኝ ወራት እቅድ አፈጻጸም ላይ ውይይት አደረጉ።
መድረኩን በንግግር የከፈቱት የኢንስቲትዩቱ ዋና ዳይሬክተር አቶ ጌታቸው ነጋሽ እንደገለጹት የዘጠኝ ወራት እቅድ አፈጻጸም ሁሉም በየዘርፉ ያከናወነው ሲሆን እንደሃገር ትላልቅ ሥራዎች የተሰሩበት እንደሆነ ገልጽዋል፡፡ ነገርግን አሁን በሰራነው ሥራ እየተኩራራን ሳይሆን በመፍጠንና በመፍጠር የኢትዮጵያን ብልጽግና እውን ለማድረግ መሥራት ይጠበቅብናል፤ የኢትዮጵያን ብልጽግና ከሚያረጋግጡት ዋና ምሶሶዎች አንዱ ደግሞ ቱሪዝም በመሆኑ የተቋማችን ድርሻ የጎላ ነው ብለዋል።
በ2017 ዓ. ም የዘጠኝ ወራት ሀገራዊ እቅድ አፈጻጸም ሪፖርቱን ያቀረቡት የኢንስቲትዩቱ የጥናት ምርምርና ማማከር ዘርፍ ም/ዋና ዳይሬክተር አቶ ይታሰብ ስዩም ባቀረቡት ሰነድ ባላፉት ቱሪዝም አንዱ የኢኮኖሚ ምሶሶ ተደርጎ በመያዙ የቱሪዝም አቅሞቻችን በማጎልበት የኢኮኖሚ ተጠቃሚነትን ማረጋገጥ እንደሚቻል ተገልጿል፡፡
አዳዲስ መዳረሻዎች ተገንብተዋል፣ ነባሮቹ ጥገና ተደርጎላቸዋል፣ ሁነት የማስተናገድ አቅማችንን የሚያሳድጉ ትላልቅ የመሰብሰቢያ ማዕከላት መገንባታቸውን እንግዳን በጥሩ ስነምግባር ማስተናገድ የሚችሉ ባለሙያዎችን ማፍራታችን እንደማሳያ ጠቅሰው የአፍሪካ ህብረት የመሪዎች ጉባኤ በጥሩ ሁኔታ መጠናቀቁን በጥሩ ጎን የሚታይ ነው ብለዋል፡፡
በሌላም በኩል በአፈፃፀም ሪፖርቱ እንደተገለፀው በዓለም አቀፍ ደረጃ እየታየ ያለው የዋጋ ግሽበት እንዲሁም የንግድ ጦርነት ኢትዮጵያ ላይ የሚኖረውን ጫና ለመከላከል የኢትዮጵያን የተወዳዳሪነት አቅሞ ማጎልበት፣ አማራጭ የኢንቨስትመንት መዳረሻ የሚያደርጉ ተግባራት ላይ ማተከኮር እንደሚገባ ሰነዱ ይጠቅሳል።
ከሥራ እድል ፈጠራ እና ከሪፎርም ጋር የተጠቀሱ ዘርዘር ያሉ ጉዳዮች ሲኖሩ በሀገር ውስጥ 3.14 ሚሊዮን ለሚሆኑ ዜጎች የሥራ ዕድል ተፈጥሮላቸዋል ተብሏል።
ሪፖርቱ ስድስት ዋናዋና ክፍሎች የያዘ ሲሆን የዓለም አቀፍ ኢኮኖሚ አዝማሚያና በኢትዮጵያ ላይ ያለው አንድምታ፣ የማክሮ ኢኮኖሚ እና ሪፎርም፣ የመሰረተ ልማት ዘርፍ አፈጻጸም፣ ማህበራዊ ዘርፍ፣ ሰላምና ዲፕሎማሲ እና ትኩረት የሚሹ ጉዳዮች በዝርዝር ቀርበዋል፡፡
ከቤቱም በጥያቄና በአስተያየት ሃሳቦች የተነስተው ውይይት ተደርጎባቸዋል።
ትክክለኛ መረጃዎችን ለማግኘት የሚከተሉትን ማስፈንጠሪያዎች ይጠቀሙ
ፌስቡክ፡ https://www.facebook.com/tticommunication
ቴሌግራም ፡https://t.me/tticommunication
ዌብሳይት፡ https://www.tti.edu.et


Recent Comments