መጋቢት 29/2015 ዓ.ም የቱሪዝም ማሰልጠኛ ኢንስቲትዩት አመራርና ሰራተኞች በወቅታዊ ሀገራዊ ጉዳይ እና በመንግስት እየተካሄዱ ያሉ የልማት እንቅስቃሴዎች እንዲሁም ከሰላም፣ ከኑሮ ውድነት እና ሌሎች ወቅታዊ ሀገራዊ ጉዳዮች ጋር የተያያዙ አጀንዳዎች እንዲሁም ህብረተሰቡ እየገጠመው ያለውን የኑሮ ጫና ለማቃለል እየተሰሩ ያሉ ስራዎች ተነስተው ውይይት ተደርጎባቸዋል፡፡
የመድረኩን አስፈላጊነትና ዓላማ በመግለፅ ውይይቱን ያስጀመሩት የኢንስቲትዩቱ ዋና ዳይሬክተር አቶ ጌታቸው ነጋሽ ሲሆኑ ለውይይት የተዘጋጀውን ሰነድ የተቋሙ አመራርና አስተዳደር ዘርፍ ም/ዋና ዳይሬክተር አቶ ገዛኸኝ አባተ አቅርበዋል፡፡
በሀገራችን የለውጥ ጉዞ የተገኙ ስኬቶች፣ ያጋጠሙና እያጋጠሙ ያሉ ፈተናዎች በሰነዱ ተዳሷል። ኢትዮጵያ በተለያዩ ፈተናዎች ውስጥ ሆና በርካታ ስኬቶችን እያስመዘገበች የምትገኝ መሆኗ፤ ችግሮችን በጥበብ በመፍታት የሀገርን ሉአላዊነት የሚፈታተኑ አደጋዎችን
የመቀልበስ፣ ከስንዴ ምርትና ተያይዞ በምዕራቡ ዓለም አገራችን የፈጠረችው የገጽታ ግንባታ፣ አሉታዊ የሆኑ አመለካከቶችን በማክሸፍ መለወጥ እንደሚቻል ያመላከተ መሆኑ ሰነዱ ተገልጿል፡፡
የዜጎችን ደህንነት ማስጠበቅ፣ የህግ የበላይነት ማስፈን፣ የሀገር ውስጥ ምርትን ማሳደግ፣ የመሳሰሉት በቀጣይ ትኩረት የሚሹ ጉዳዮች ሆነው ተነስተዋል፡፡
በሠራተኛው በኩልም በቀረበው ሰነድ ውይይት ተደርጎ ጥያቄና አስተያየት ተሰጥቷል ‘ህዝባዊ ውይይቶች ሊጠናከሩ ይገባል’ ህዝቡ ሰላሙን ጠብቆ የዕለት ተዕለት ኑሮውን አሸንፎ መኖር ነው የሚፈልገው ብለዋል ተሳታፊዎቹ፡፡
ሚዲያዎች የህዝብን ስሜት በመረዳት ፈጣን፣ ወቅታዊና ሚዛናዊ መረጃ ለህዝቡ ተደራሽ እንዲያደርጉ በመንግስት በኩል ሊሰራ ይገባል በማለት ሰራተኛው አስተያየት ሰጥቷል፡፡
ኢንስቲትዩቱ በቀጣዩ ቀን ከሰራተኛው ጋር የዘጠኝ ወር ዕቅድ አፈፃጸሙን ይገመግማል፡፡

Recent Comments