ለቱሪዝም ማሰልጠኛ ኢንስቲትዩት አሰልጣኞች የማስተማር ስነ ዘዴ ስልጠና ተሰጠ ።

ቱሪዝም ማሰልጠኛ ኢንስቲትዩት የሰልጣኞችንና የስልጠና እርካታ ለማሻሻል እንዲሁም የኢንዱስትሪውን ፍላጎት በዕውቀት በክህሎትና በስነምግባር የተደራጀ ባለሙያ ለማቅረብ የሚያስችል የማስተማሪያ ስነ ዘዴ ስልጠና ተሰጣቸው ።
በመክፈቻው የተገኙት የተቋሙ የስልጠናና አቅም ግንባታ ምክትል ዋና ዳይሬክተር አቶ ሀብታሙ ክብረት እንደገለጹት ይህ ስልጠና አዲሱን የትምህርት ፖሊስ ወደተግባር ለመቀየር የሚረዳ መሆኑን በመጠቆም 12ኛ ክፍል የጨረሰ ተማሪ የእጅ ሙያ ይዞ የሚመረቅ እንደሆነ አዲሱ ትምህርት ፖሊስ ይገልጻል። እነዚህ ተማሪዎችን በፍላጎታቸው ወደ ቴክኒክና ሙያ ኮሌጆች ሲመጡ ተማሪ ተኮር በሆነ ስነ ዘዴ ለማስተማር ይህ ስልጠና አስፈላጊነት የጎላ ነው ብለዋል።
ቱሪዝም ማሰልጠኛ ኢንስቲትዩት የልህቀት ማዕከል ሆኖ ለመገኘት የመምህራን አቅም ግንባታ ወሳኝ በመሆኑ ከእስትሪፕ (EASTRIP )ፕሮጀክት ጋር በመተባበር የተለያዩ ስልጠናዎች ልምድ ልውውጦች በቀጣይ እንደሚኖሩ አቶ ሀብታሙ ክብረት ተናግረዋል።
ይህን ሰልጠና በጥሩ ስነምግባር መከታታል እንዳለባቸው አሳስበዋል።
የስልጠናው ዓላማ የተቋሙን ገጽታ ለመገንባት ፣ የኢንዱስትሪውን ፍላጎት በዕውቀት በክህሎትና በስነምግባር የተደራጀ ባለሙያ ለማቅረብ ሲሆን ይህም ስልጠና በተለያዩ ምርምር ውጤቶችና ስብሰባዎች ከተገኙ መነሻ ሀሳብ ተወስዶ እንደሆነ የኢስትሪፕ(EASTRIP) ፕሮጀክት አስተባባሪ አቶ አብርሃም ለገሰ ተናግረዋል።
ይህ ፕሮጀክት የተቋሙን ወደልህቀት በሚያደርሱ ሥራዎችና የአሰልጣኞችን አቅም ግንባታ በጥናት ላይ በመመሥረት የሚሰራ በመሆኑ የታዩትን ክፍተቶች ለመሙላት ከሌሎች ተቋማት የጋር ስራዎችን ይሰራል ።
ስልጠናውን የሰጡት ከፌዴራል ቴክኒክና ሙያ ኢንስቲትዩቱ የካሪኩለምና ኢንስትራክሽን ረዳት ፕሮፌሰር ዶ/ር አለማየሁ ሀብቴ እና የካሪኩለምና ኢንስትራክሽን ሌክቸር አቶ ንጉሤ ኦሎሎ ናቸው።
ሌላው የኮርስ ካታሎግ ማሻሻያ፣ የሪጂስተራር አሰራሮችን በተመለከተና የኳሊቲ አሹራንስ ሥራዎች ማሻሻያ እየተደረገ ነው። ማሻሻያ የሚደረግባቸው ከዚህ በፊት የሚነሱ ውስንነቶችን ማስተካከል ባለባቸው ጉዳዮች በመወያየት ውሳኔ ሀሳብ ላይ እንደሚደረስ የአጠቃላይና ደጋፊ ትምህርት አስተባባሪ አቶ ዋቅጅራ ረቡማ ተናግሯል።
እነዚህ ስራዎች ሁሉ ተቋሙ ወደ ልህቀት ማዕከልነት የሚያደርገውን ጉዞ የሚያስፈፅሙ ተግባራት ናቸው። ይህም አቅም ግንባታ ስራ በዚህ የሚያበቃ አለመሆኑ በአስተባባሪው ተገልጿል።