በሆቴልና በቱሪዝም ዘርፍ የዲግሪ ካሪኩለም ማሻሻያ እና የክህሎት ውድድር ማስፈጸሚያ ሰነድ ተዘጋጀ።

በቱሪዝም ማሰልጠኛ ኢንስቲትዩት በሆቴልና በቱሪዝም ዘርፍ የዲግሪ ካሪኩለም ማሻሻያ እና የክህሎት ውድድር ማስፈጸሚያ ሰነድ ተዘጋጀ። የተቋሙ የትምህርትና ስልጠና ዘርፍ ምክትል ዋና ዳይሬክተር አቶ ሀብታሙ ክብረት እንደገለጹት ከዚህ በፊት የክህሎት ውድድር የሚካሄድ ቢሆንም ደረጃውን የጠበቀ ሰነድ ባለመኖሩ ወጥ ውድድር እንዳልነበረ በመጠቆም ውድድሮቹ በቋንቋም እንዲደገፉ በማድረግ ቀጣይ የሚኖሩ የክህሎት ውድድሮችን በተሳካ ሁኔታ ለማሰፈጸም የሚረዳ ሰነድ ማዘጋጀት እንዳስፈለገ ተናግረዋል።
በመቀጠልም የካሪኩለም ዝግጅቱን በተመለከተ የተቋሙ ምርምርና ማማከር ዘርፍ ምክትል ዋና ዳይሬክተር አቶ ይታሰብ ስዩም እንደተናገሩት ካሪኩለም ማሻሻያ ያስፈለገው ከዚህ በፊት ከሌሎች ኮፒ ተደርጎ ይሰራበት እንደነበረና አሁን ተቋሙ ተግባር ተኮር በመሆኑ የትምህርትና ስልጠና ፖሊስ ምክንያት እንዲሁም በቅርቡ ተቋሙ ያጠናቸው ጥናቶች ለዚህ ካሪኩለም ማሻሻያ መነሻ መሆናቸውን ገልጸዋል።
በሰነድ ዝግጅቱ አምስት ኮርሶች ለኢንዱስትሪው እንደሚቀርቡ ተጠቅሟል።
በሁለቱም ሰነድ ዝግጅቶች ላይ ከሥራና ክህሎት ሚኒስቴር ካሪኩለም ዝግጅት ከፍተኛ ባለሙያዎች እና የኢንዱስትሪው ባለቤቶች ተሳትፈውበታል።
ሁል ጊዜ በተቋሙ የሚሰጠውን የስልጠና ጥራት ለማሻሻል እንዲሁም የተቋሙን ገጽታ ለመገንባት የሚያግዘው EASTRIP ፕሮጀክት ጋር በመተባበር እንደሆነ ተገልጿል።
ውድ የገጻችን ተከታዮች ላይክና ሼር በማድረግ መረጃዎችን ተደራሽ እንድታደርጉልን እንጠይቃለን።