ጥራትን መሠረት ያደረገ ኦዲትና የግለ ግምገማ ሪፖርት አዘገጃጀትና አሰራር ዙሪያ የግንዛቤ ማስጨበጫ ስልጠና ተሰጠ። ቱ .ማ .ኢ የፌዴራል ቱሪዝም ማሰልጠኛ ኢንስቲትዩት ከትምርህት እና ስልጠና ባለስልጣን ጋር በመተባበር ያዘጋጀው ለትምህርት ክፍል ኃላፊዎች ፣ሥራ አስፈጻሚዎች እና ባለሙያዎች ጥራትን መሠረት ያደረገ የኦዲት አሰራር እና ስለ ግለ ግምገማ ዝግጅት ስልጠና ተሰጠ።

የፕሮግራም መክፈቻ ንግግር ያደረጉት የኢንስቲትዩቱ ም/ዋና ዳይሬክተር አቶ ገዛኸኝ አባተ ተቋማችን በሚሰጠው ስልጠና ጥራትን በማስቀደም ፣ ፍላጎትን መሠረት ያደረገ እና በባለድርሻ አካላት ተሳትፎ የዳበረ እንደሆነ ገልጸው ከጊዜ ወደጊዜ የሥልጠና ጥራትን ለማስጠበቅ የሚያስችሉ የአሰራር ስርዓቶችን እየተተገበሩ ስለመሆኑ ISO21001:2018 እውቅና ማግኘታችን እንደ አንድ ማሳያ አንስተዋል።
ዛሬ የሚሰጠውን ስልጠና በትኩረት በመሳተፍ አስፈላጊውን መረጃ በማደራጀት ወደ ውጤት እንዲያሻግሩ ለተሳታፊዎቹ መልእክት አስተላልፈዋል።
ስልጠናውን ከትምህርት እና ስልጠና ባለስልጣን በመጡ ባለሙያዎች ወ/ሮ ምስራቅ አሰፋ እና አቶ ግርማ አበበ ተሰጥቷል።
የስልጠናው ዓላማ ጥራትን መሠረት ያደረገ ኦዲትና የግለ ግምገማ ሪፖርት አዘገጃጀትና አሰራር ዙሪያ ግንዛቤ የሚያስጨብጥ ሲሆን ከስታንዳርዶችና ከማስፈፀሚያ ስልቶች አንፃር ምን እንደሚመስሉ በተግባር ልምምድ እንዲዳብሩ ተደርጓል።
ትክክለኛ መረጃዎችን ለማግኘት የሚከተሉትን ማስፈንጠሪያዎችን ይጠቀሙ
ፌስቡክ፡ https://www.facebook.com/tticommunication
ቴሌግራም ፡https://t.me/tticommunication
ዌብሳይት፡ https://www.tti.edu.et