የማሰልጠኛ ማዕከሉ የሲዳማ ክልል ቱሪዝምን ለማሳደግ ላበረከተው አስተዋጽኦ ምስጋና ተቸረው።

የሆቴልና ቱሪዝም ሥራ ማሰልጠኛ ማዕከል የክልሉን ቱሪዝም ለማሳደግ እና በዓለም ቱሪዝም ቀን አከባበር ላበረከተው አስተዋጽኦ ከክልሉ ፕሬዝዳንት አቶ ደስታ ሌዳሞ የምስጋና የምስክር ወረቀት ተበርክቶለታል።
ማዕከሉ ከሲዳማ ክልል ባህልና ቱሪዝም ቢሮ ጋር በመተባበር የመጀመሪያ የሆነውን የክልሉን የቱሪስት ማፕ፣ የሲዳማ ክልልን በአዲስ መልክ ማስተዋወቅ ላይ ያተኮረ ጥናት መስራቱ፣ የሲዳማ ባህላዊ ምግቦች ደረጃውን የጠበቀ የምግብ አሰራር ሂደት (standardized recipe) ማዘጋጀቱ ለክልሉ ከፍተኛ እገዛ መሆኑ በምስጋና መርሃግብሩ ላይ ተገልጿል።