ላለፉት ሀምሳ ዓመታት በሆቴልና ቱሪዝም የስልጠና መስክ ፋና ወጊ የሆነው የሆቴልና ቱሪዝም ሥራ ማሰልጠኛ ኢንስቲተዩት በሆቴልና ቱሪዝም የስልጠና መስኮች ከደረጃ አንድ እስከ አምስት በቀንና በዲግሪ በማታ የስልጠና መርሐግብር ምዝገባ መጀመራቸንን እናበስራለን፡፡
ተቋሙ በቀን መርሃግብር የ2011 ዓ.ም የ12ኛ ክፍል አጠናቀው ለቴክኒክና ሙያ የሳይንስና ከፍተኛ ትምህርት ተቋማት ሚኒስቴር ባወጣው መስፈርት መሰረት የሁሉም ክልሎችና ለድሬደዋ ከተማ አስተዳደር ትምህርት ፈላጊዎች በየክልላችሁ የሚገኙ የባህልና ቱሪዝም ቢሮዎች በሚያሳውቁት የምልመላ ጣቢያ እንድትመዘገቡ ጥሪያችንን እያስተላለፍን አዲስ አበባ ለሚገኙ ከሜክስኮ ወደ ቄራ በሚወስደው መንገድ ገነት ሆቴል አጠገብ በሚገኘው የኢንስቲትዩቱ ዋና ግቢ ከመስከረም 26 እስከ ጥቅምት 05/2012 ዓ.ም ድረስ እንድትመዘገቡ እናሳውቃለን፡፡
በማታ በሆቴል ማኔጅመንት እና በቱሪዝም ማኔጅመንት የዲግሪ ፕሮግራም ምዝገባ መጀመራችንንም እናሳውቃለን፡፡
 ለበለጠ መረጃ የተቋሙን ድረገጽ www.tti.edu.et ወይም
የስልክ ቁጥር 011 530 81 03 ደውለው መጠየቅ ይችላሉ፡፡
የሆቴልና ቱሪዝም ሥራ ማሰልጠኛ ኢንስቲትየዩት