የካቲት 22/2011 ዓ.ም ለሆቴልና ቱሪዝም ሥራ ማሰልኛ ኢንስቲትዩት ሰራተኞች የተቀናጀ የመንግስት ፋይናንስ አሰራር መረጃ ስርዓት (Integrated Financial Management Information System (IFMIS)) ዙሪያ የግንዛቤ ማስጨበጫ ስልጠና ተሰጥቷል፡፡
የተቀናጀ የመንግስት ፋይናንስ አሰራር መረጃ ስርዓት (IFMIS) በፌደራል መንግስትና በአንዳንድ ክልል ቢሮዎች ከዛሬ አስር ዓመት በፊት ጀምሮ በሙከራ ትግበራውን የጀመረ ሲሆን በአሁኑ ጊዜ ከ90 በላይ ተቋማት የፋይናንስ፣ የበጀት አሰራርን ወደ ዲጅታል በመቀየር የፋይናንስና ንብረት አስተዳደርን ውጤታማ ለማድረግ የሚያስችል ዘመናዊ የአሰራር ሂደት ነው፡፡
ቴክኖሎጂው በአሜሪካና በተወሰኑ የአፍሪካ ሀገራት ተግባራዊ የተደረገ ሲሆን የሆቴልና ቱሪዝም ሥራ ማሰልኛ ኢንስቲትዩትም በዚህ ፕሮጀክት ስራ ለመጀመር የሚያስችለውን የባለሙያ ስልጠና እየተወሰደ ይገኛል፡፡
ቴክኖሎጂው የኢንተርኔት፣ኮምፒዩተርና በዚህ ዘርፍ ስልጠና የወሰደ ባለሙያ የሚፈልግ ሲሆን የኢንፎርሜሽን ቴክኖሎጂ ባለሙያዎች መኖር ግድ ይላል፡፡
ፕሮጀክቱን ተግባራዊ ያደረጉ ተቋማት የኔትዎርክ እና የባለሙየ መቀያየር እንደችግር የሚገጥሙ እንደሆነ ስልጠኛውን የሰጡት በገንዘብ ሚኒስቴር የIFMIS ፕሮጀክት ጽ/ቤት የለውጥ ኮሚዩኒኬሽን ቡድን መሪ አቶ ቅባቱ ሰይፉ ገልጸዋል፡፡
የሆ.ቱ.ሥ.ማ.ኢ ዋና ዳይሬከተር ወ/ሮ አስቴር ዳዊት በበኩላቸው ለፕሮጀክቱ ተግባራዊነት የተቋሙ አመራርና ሰራተኞች የበኩላቸውን አስተዋጽኦ እንደሚያበረክቱ ያላቸውን እምነት ገልጸዋል፡፡