መጋቢት 30/2015 ዓ ም ቱሪዝም ማሰልጠኛ ኢንስቲትዩት ለኢንስቲትዩቱ አመራር፣ አሰልጣኞች እና ሰራተኞች የሥራ ተነሳሽነትን የሚጨምሩ፣ ሀገር መውደድና ሰውን ማክበር ለጤናማ የሥራ ግንኙነትና ለህይወት ያለውን ጠቀሜታ የሚገልጹ በተለያዩ የሙያ መስኮች የስልጠና ልምድ ያላቸውን ባለሙያዎች በመጋበዝ ስልጠና አንዲወስዱ ተደርጓል፡፡

የመጀመሪያው የ21ኛው ክፍለ ዘመን ክህሎት ወይም ተግባቦት ምን ይመስላል እኛ የት ላይ ነን የሚል ስልጠና የሰጡት ዶክተር ሀብታሙ ሙሉጌታ ናቸው። ከሰዎች ጋር ለመግባባት ሦስት መሠረታዊ ነገሮች ያስፈልጉናል እነዚህም (3Ls) ይባላሉ አንደኛው Learning skills, Life skills, literacy skill ይባላሉ።
ከሁሉ በላይ ቋንቋ ለሥራችን መሠረት ነው። ይህም ፊትን በማየት የጥያቂያችን 55% በአነጋገር ለዛ አክብሮቱ ድምፅቱ ደግሞ 38% ሲሆን ዋናው ጥያቄ 7% ይሆናል። ስለዚህ ተግባቦት ከፍተኛ ድርሻ እንደሚይዝ በአሰልጣኙ ተገልጿል።
ሁለተኛው ስልጠና የሰጡት አቶ ናትናኤል ጥሩነህ ሲሆኑ ስለ ሥራ ቦታ ዲሲፕሊን ግንዛቤ የሚያስጨብጥ ስልጠና ሰጥተዋል። በቡድን አባላት መካከል መከባበር ሲኖር ውጥረት ይቀንሳል፤ የተሻለ ምርታማነት ይጨምራል፣ ለራሳችንም ሆነ ለተቋሙ የሚጠቅም ሥራ ማስራት የሚያስችል አቅም ይፈጥራል። ይህን በምሳሌ ሲያስረዱ
አንበሳ ሁልጊዜ ንጉስ የሆነው በአመለካከቱ ነው፤ ይህም በውስጡ ፍርሃት የለሽ ተነሳሽነት ፣ እርግጠኝነት ሃላፊነት መውሰድ ባለቤትነት ይታይበታል፣ ነፃነትና ብቃት አለው፤ የፈለገውን ነገር በየትኛውም መልኩ ሳያሳካ አይመለስም። በሌላ በኩል ችግሮች ሲገጥሙን ለመፍታት ከንስር መማር ይቻላል ሲሉ በተለያዩ ምሳሌዎች አቶ ናትናኤል ገልጸ አድርገዋል ።
ሦስተኛው አሰልጣኝ የማህበራዊ ዘርፍ አማካሪ አቶ አምባላይ ዘርዓይ ይባላሉ።
ስለ ግጭትና ግጭት አፈታት ዘዴዎች ገለፃ አድርገዋል፡፡ በተጨማሪም ስለ ሀገር ፍቅር/መውደድ መሠረታዊ ነገሮችን አንስተው በተለያዩ ምሳሌዎች ማብራሪያ ሰጥተዋል፡፡
ራስን በሀገር መግለጽ “ እኔ ኢትዮጵያዊ ነኝ” የሚውን በተግባር መግለጽ፣ ራስን አሳልፎ ለመስጠት ዝግጁ መሆን፤ በተጨማሪም የሀገር ፍቅር የሚያስፈልገው ለአብሮነት መሠረት ስለሆነ ነው። መልካም ባህርይ ወይም ስብዕና ችግሮችን የማለፊያ አንዱ መንገድ እንደሆነ አቶ አምባላይ ተናግረዋል።
በመጨረሻም የተቋሙ የሥልጠና ዘርፍ ምክትል ዋና ዳይሬክተር አቶ ሀብታሙ ክብረት ሁሉንም አሰልጣኞችና ስልጠናውን በአግባቡ የተከታተሉ ሰራተኞችን በማመስገን ስልጠናዎቹ ቀጣይነት እንደሚኖራቸው በመጠቆም የስልጠናው ውጤትም በቀጣይ የሚታይ እንደሚሆን ገልጸዋል።