ታህሳስ 26/2015 ዓ.ም ቱ. ማ. ኢ ቱሪዝም ማሰልጠኛ ኢንስቲትዩት በቂርቆስ ክፍለ ከተማ ወረዳ 11 ለሚገኙ ሥራ አጥ ሴቶች በሆቴልና ቱሪዝም ዘርፎች ያሉ መልካም አጋጣሚዎችን የሚያሳውቅ የግንዛቤ ማስጨበጫ ስልጠና ተሰጣቸው፡፡
በስልጠናው አንድ መቶ ያህል ሥራ አጥ ሴቶች የተሳተፉ ሲሆን ስልጠናውን የሰጡት የቱሪዝም ትምህርት ክፍል አስተባባሪ አሰልጣኝ አቢይ ንጉሴ የቱሪዝም ዘርፉን በተመለከተ ሲሆን ፤ የእንግዳ አቀባበልና መስተንግዶ ትምህርት ክፍል አስተባባሪ አሰልጣኝ ህይወት ጥበቡ በእንግዳ አቀባበልና መስተንግዶ ዘርፍ ስልጠና ሰጥተዋል፡፡

ይህ ስልጠና ሰልጣኞች በሆቴልና በቱሪዝም ዙሪያ ስላሉ የሥራ ዕድሎች ግንዛቤ አግኝተው በቀጣይ በሚደረጉ ስልጠናዎች ፍላጎታቸውን ለይተው እንዲሰለጥኑ የሚያስችል መሆኑ ተገልጿል፡፡