ቱ. ማ .ኢ .ጥቅምት 25/2014 ዓ.ም ስልጠናውን በንግግር የከፈቱት የተቋሙ ዋና ዳይሬክተር ወ/ሮ አስቴር ዳዊት ሰልጣኞች ከመደበኛ ትምህርታቸው በተጨማሪ
በተለያዩ ክበባት በመሳተፍ ከመጡበት የተለያየ ይዘውት የመጡትን ልምድ ለሌሎች ለማካፍል ምቹ ሁኔታ የሚፈጥር መሆኑን በመጠቆም ሥልጠናው በጥሩ ሥነምግባር የታነፃችሁ ሆናችሁ የተሻለ የትምህርት ተሳትፎ እንዲኖራችሁ የሚያደርግ ስለሆነ በአግባቡ እንድት ከታተሉ በማለት መልዕክታቸውን አስተላልፈዋል፡፡
የመጀመሪያውን ስልጠና የሰጡት መምህር ታረቀኝ መኮንን የክበባት እንቅስቃሴ በክፍል ውስጥ ከሚሰጥ ትምህርት በተጫማሪ እራስን ለማብቃትና ለተግባቦት እንደሚጠቅም ሰፊ ማብራሪያ ሰጥተዋል፡፡
መምህር ሞኮንን ጋሻው በበኩላቸው ሰልጣኞች በትምህርታቸውም ሆነ በኑራቸው በራስ መተማመን እንዲያዳብሩና ሁልጊዜም የህይወት መርሆዋቸው እችላለሁ እንዲሉ የሚያደርግ የማነቃቂያ ስልጠና ሰጥተዋል፡፡
በተጨማሪም የተቋሙ ስነ- ምግባርና ጸረ-ሙስና ዳይሬክቶሬት አቶ ታምራት ተፈራ ለሰልጣኞች የተቋሙን ስነምግባር ደንብን፣ ከሰልጣኞች የሚጠበቀው መብትና ግዴታቸውንም ጭምር በስፋት በማንሳት ስልጠና ሰጥተዋል፡፡፡፡
በመጨረሻም የተማሪዎች ፕሬዝዳንት በመምረጥና በተለያዩ ክበባት በማደራጀት ስልጠናው ተጠናቋል ሰብሳቢዎች በመምረጥ ተጠናቋል ፡፡