ቱ.ማ.ኢ መጋቢት 08/2016 ዓ.ም የቱሪዝምና ማሰልጠኛ ኢንስቲትዩት ከEASTRIP ፕሮጀክት ጋር በመተባበር የሴት ሠራተኞችን አቅም ለማጎልበት የሚያስችል ስልጠና ተሰጥተዋል።

ስልጠናው የደንበኛ አገልገሎት አሰጣጥ እና የተግባቦት ክህሎትን ማዳበር ፣ የግልና የሥራ አካባቢ ንጽህናና ጤና አጠባበቅ እንዲሁም የቢሮ አያያዝ ላይ ያተኮረ ነው።
ስልጠናውን የተለያዩ በዘርፉ ልምድና የትምህርት ዝግጅት ያላቸው አሰልጣኞች ለተከታታይ ሶስት ቀናት የተሰጠ ሲሆን፤
ስልጠናው የሴቶችን አቅም ከማሳደግ አንፃር ያለው አስተዋጽኦ ከፍተኛ መሆኑን የገለጹት ተሳታፊዎች በቀጣይ የአገልግሎት ጥራትን በማሻሻል የደንበኞችን እርካታን ለመጨመርና አገልግሎት ላይ የሚከሰቱ ችግሮችን ለመፍታት ችሎታቸውን ለማሳደግ እንደሚያግዛቸው ተናግረዋል፡፡
ትክክለኛ መረጃዎችን ለማግኘት የሚከተሉትን ማስፈንጠሪያዎችን ይጠቀሙ
ፌስቡክ፡ https://www.facebook.com/tticommunication
ቴሌግራም ፡https://t.me/tticommunication
ዌብሳይት፡ https://www.tti.edu.et/