ቱ ማ ኢ ግንቦት 17/2017 ዓ.ምቱሪዝም ማሰልጠኛ ኢንስቲትዩት በዓለም ቅርስነት በተመዘገበው የጢያ ትክል ድንጋይ ለቱሪስት አገልግሎት በመሰረታዊነት የሚያስፈለጉ መረጃ ዴስክ፣ የሥጦታ እቃዎች መሸጫ፣ ቱሪስት የሚያርፍበት መለስተኛ ካፌ እና መፀዳጃ ቤት መስሪያ የሚሆን ስፋቱ 200 ካሬ ቦታ ርክክብ አደረገ፡፡ የኢንስቲትዩቱ ዋና ዳይሬክተር አቶ ጌታቸው ነጋሽ እንደገለጹት የቱሪስት ሳይቶችን ለመደገፍ ስናስብ ቀዳሚ ያደረግነው ጢያ ሲሆን ይህ የጉብኝት ቦታ የሚመጡ ጎብኚዎችን ታሳቢ ማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ፣ የዞንና የወረዳ አመራሮች ጋር በመነጋገር የቦታ ችግሮች ተፈቶ ቀጣይ ወጣቶችን የማደራጀት ሥራ በወረዳው እንዲከናወን በማሳሰብ በአጭር ጊዜ ግንባታው እንደሚጠናቀቅ ገልጸዋል።
የተቋሙ ጥናትና ምርምር ዘርፍ ም/ዳይሬክተር አቶ ይታሰብ ስዩም እንደተናገሩት ግንባታው ለወጣቶች እና ሴቶች የሥራ እድል የሚፈጥር ብለዋል፡፡
ጢያ በዓለም አቀፍ ቅርስነት ከተመዘገቡ ቅርሶች አንዱ በመሆኑ ግንባታው ለሀገር ውስጥና ለውጭ ጎብኝዎች የእንግዳ መቀበያና የመጸዳጃ ችግሮችን የሚፈታ ሲሆን እዚህ ቦታ ተደራጅተው ሥራ ለሚጀምሩ ወጣቶች በተለያዩ ዘርፎች በስልጠና እንደሚደግፉ ቃል ተገብቷል።
ግንባታው በአንድ ወር ጊዜ ውስጥ ተጠናቆ ሥራ እንደሚጀምርም ተገልጿል።
በርክክቡ የተገኙት የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ባህል ቱሪዝም ቢሮ ምክትል ሀላፊ አቶ ኑር ከድር ቱሪዝም ማሰልጠኛ ኢንስቲትዩቱ ማዕከላዊ ኢትዮጵያ ከተቋቋመበት ጊዜ ጀምሮ በጥናትና ምርምር በስልጤ ዞን የሚገኙ ባህላዊ ምግቦችና መጠጦች በተለያዩ ሆቴሎች በምግብ ዝርዝር ላይ እንዲመዘገብ በማድረግ እና የቱሪዝም ማፕ ለዞኑ በመስራታቸው አመስግነው አሁንም በዚህ ትልቅ እድል ጢያን ምርጫችሁ ስላደረጋች እናመሰግናለን ብለዋል።
በርክክቡ የዞንና የወረዳ ከፍተኛ አመራሮች ተገኝተዋል።
በተጨማሪም ቱሪዝም ማሰልጠኛ ኢንስቲትዩት በ2014 ዓ ም እና 2015 ዓ ም በአርንጓዴ አሻራ መርሐ ግብር የተተከሉ ችግኞችን ጎብኝተዋል።
ትክክለኛ መረጃዎችን ለማግኘት የሚከተሉትን ማስፈንጠሪያዎችን ይጠቀሙ
ፌስቡክ፡ https://www.facebook.com/tticommunication
ቴሌግራም ፡https://t.me/tticommunication
ዌብሳይት፡ https://www.tti.edu.et


Recent Comments