ታህሳስ 23/2015 ዓ.ም ቱሪዝም ማሰልጠኛ ኢንስቲትዩት ከኢትዮጵያ ሴንተር ፎር ዴሴብሊቲ ዴቨሎፕመንት (ECDD) ጋር በመተባባር ለአካል ጉዳተኞች በቱሪዝም ዘርፍ ሥልጠና ተሰጠ፡፡
አካል ጉዳተኞች አቅማቸው የሚችለውን ሥራ በተለይም በቱሪዝም መስክ የተለያዩ የስራ ዘርፎች ላይ መሰማራት የሚያስችላቸው የግንዛቤ ሥልጠና የተሰጣቸው ሲሆን በቱሪዝም መዳረሻ ሥፍራዎችና በሆቴሎች በቀላሉ ሊሰሯቸው የሚችሏቸውን በምስል ጭምር የተደገፈ ስልጠና ተሰጥቷቸዋል፡፡
ቱሪዝም በባህሪው ለብዙዎች የሥራ ዕድል መፍጠር የሚችል ሲሆን አካል ጉዳተኞችንም የዚህ የሥራ ዕድል ተጠቃሚ ማድረግ እንደሚቻል ስልጠናውን የሰጡት የቱሪዝም አሰልጣኝ አቶ ፍሬው አበበ ገልጸዋል፡፡
ኢንስቲትዩቱ በማህበረሰብ አቀፍ አገልግሎት የተለያየ እገዛ ለሚያስፈልጋቸው የህብረተሰብ ክፍሎች ድጋፍ እያደረገ እንደሆነ ይታወቃል፡፡
እነዚህ በስልጠናው የተካተቱት አካል ጉዳተኛ የህብረተሰብ ክፍሎች ወደፊትም በአካታች ቱሪዝም (Inclusive Tourism) በአቅማቸው ሊሰሯቸው የሚችሏቸውን የፍላጎት ዳሰሳ መሰረት በማድረግ ስልጠናው የሚቀጥል ይሆናል፡፡
Recent Comments