ለኢንስቲትቱ መምህራን በቴክኖሎጂ ሽግግር ዙሪያ ስልጠና ተሰጠ፡፡
ሆ.ቱ.ሥ.ማ.ኢ ታህሳስ 12/2011 ዓ.ም
ለሆቴልና ቱሪዝም ሥራ ማሰልጠኛ ኢንስቲትዩት መምህራን የቴክኖሎጂ ሽግግር ጽንሰሃሳብ ዙሪያ ስልጠና ተሰጠ፡፡
ስልጠናው በሆቴልና ቱሪዝም ዘርፍ የሚውሉ አዳዲስ ቴክኖሎጂዎችን ለመምረጥና ለማሻገር የሚያስችል ግንዛቤን ለመፍጠር ታቅዶ የተዘጋጀ መሆኑን የምርምርና ማማከር አገልግሎት ክፍል አስተባባሪ አቶ ማዘንጊያ ሺመልስ ገልጿል፡፡
አቶ ማዘንጊያ በቀጣይ መምህራን አቅማቸውን በመገንባት ለዘርፉ እድገት ጠቃሚ የሆኑ አዳዲስ ቴክኖሎጂዎችን መርጠው ማሸጋገር ያስፈልጋል ብሏል፡፡
በስልጠናው ላይ የተሳተፉት አሰልጣኞችም ስልጠናው አዳዲስ የቴክኖሎጂ ሽግግርን ለማድረግ እንደሚረዳም በሰልጠናው ወቅት ገልጸዋል፡፡
ስልጠናው ለሶስት ቀናት የቆየ ሲሆን 40 መምህራን ተሳትፎበታል፡፡
Recent Comments