ሆ.ቱ.ሥ.ማ.ኢ መጋቢት 17/2011 ዓ.ም
ለሆቴልና ቱሪዝም ሥራ ማሰልጠኛ ኢንስቲትዩት ሰራተኞች የመጀመሪያ ደረጃ ህክምና እርዳታ የግንዛቤ ማስጨበጫ ስልጠና ተሰጠ፡፡
የመጀመሪያ ደረጃ ህክምና እርዳታ ሰዎች በየትኛውም አጋጣሚ የሚደርስባቸው አደጋ የከፋ ጉዳት እንዳያስከትል ወደ ሀኪም ቤት ሂደው ተገቢውን ህክምና እስኪያገኙ ድረስ የሚሰጠ ጊዜያዊ ህክምና ነው፡፡
ስልጠናውን የሰጡት ሲስተር ምኞት አበበ እንደገለጹት የዚህ ስልጠና ዋና ዓላማ ሰዎች የሚያጋጥማቸውን አደጋ ሙያዊ በሆነ መልኩ እርዳታ ሚሰጥ ሰው ላይ ሌላ ችግር ሳያስከትል በሰብዓዊነት የደረሰበትን ሰው መርዳት የመያስችል ነው ብለዋል፡፡ አክለውም በሀገራችንም ሆነ በሌሎች ሀገራት አደጋ የደረሰበትን ሰው መርዳት የተለመደ እና በህግም የተደነገገ በመሆኑ የመጀመሪያ ደረጃ ህክምና እርዳታ ስልጠና መውሰድ ተገቢ ነው ብለዋል፡፡
የሥልጠናው ተሳታፊዎች በበኩላቸው ማሰልጠኛ ኢንስቲትዩቱ ከዘርፉ ጋር ተዛማጅ የሆነ ህክምና እርዳታ አሰጣጥ ስልጠና የሚሰጥ ቢሆንም የአስተዳደር ዘርፍ ሰራተኞች የዚህ ስልጠና ተካፋይ መሆናችን በጣም ጠቃሚ ነው ብለዋል፡፡