ነሃሴ 22/2016 ዓ ም ለቱሪዝም ማሰልጠኛ ኢንስቲትዩት ሴት ሰራተኞች ይሰጥ የነበረው የትራንስፎርሜሽናል አመራርነት የግንዛቤ ማስጨበጫ ስልጠና ተጠናቀቀ።

በዚህ ስልጠና ማጠቃለያ የተገኙት የተቋሙ ሥራ አመራርና አስተዳደር ዘርፍ ም/ ዋና ዳይሬክተር አቶ ገዛኸኝ አባተ እንደገለጹት ሴቶች በተቋሙ ባሉት ሥራዎች ሁሉ ከፍተኛ ሚና እንዳላቸውና እነሱን ማሰልጠን የተቋሙን ማህበረሰብ ማሰልጠን እንደሆነ ተናግረዋል።
ስልጠናውን የሰጡት አሰልጣኞች ከሲቪል ሰርቪስ ወ/ሮ ሰርገወርቅ ሲሳይና ወ/ሮ ምንዳዬ ዮሐንስ ሲሆኑ በዛሬው እለት ሰሜታችንን እንዴት መቆጣጠር ፣ ራስን በማወቅ እና በመግዛት ማህበረሰብን ማወቅ እንደሚቻል፤ እንዲሁም የግንኙነት አስተዳደር በማስፋት ጥሩ ውጤት ማምጣት እንደሚቻል ስልጠና ሰጥተዋል ።
ወ/ሮ ሰርገወርቅ ለውጥ የሚጀምረው ንቁ ከመሆንና የራሰን ሰሜትና የሰዎችን በመለየት በአስፈላጊው ቦታና ጊዜ ስንጠቀም እንደሆነ ገልጸዋል።
የተቋሙ ሴቶችና ማህበራዊ ጉዳይ ሥራ አስፈጻሚ ወ/ሮ ንግስት ሲሳይ አሰልጣኞች ሰልጠናውን በትኩረት ስለተከታተሉ አመስግነው ስልጠናውን ወደተግባር መለወጥ እንዳለባቸውም አሳስበዋል
ስልጠናውን የወሰዱት ሴቶችም ስልጠናው ወቅቱን የጠበቀ መሆኑን በመግለፅ ለሴቶች ብቻ ሳይሆን ለሁሉም የተቋሙ ማህበረሰብ የሚያስፈልግ መሆኑን በመጠቆም ስልጠናውን ያዘጋጁትንን የEASTRP ፕሮጀክት አስተባባሪዎችና የተቋሙ ሴቶችና ማህበራዊ ጉዳዮች አካቶ ክፍልን አመስግነዋል።
ትክክለኛ መረጃዎችን ለማግኘት የሚከተሉትን ማስፈንጠሪያዎችን ይጠቀሙ
ፌስቡክ፡ https://www.facebook.com/tticommunication
ቴሌግራም ፡https://t.me/tticommunication
ዌብሳይት፡ https://www.tti.edu.et