ሆ.ቱ.ሥ.ማ.ማ ግንቦት 27/2013 ዓ.ም የባህልና ቱሪዝም ሚኒስቴር ከብሔራዊ ቤተ መዛግብት እና ቤተ መጻህፍት ኤጀንሲ፣ ከሆቴልና ቱሪዝም ማሰልጠኛ ማዕከል፣ ከቱሪዝም ኢትዮጵያ እና ከዱር እንስሳት ልማትና ጥበቃ ባለስልጣን ጋር በመተባበር ለሚኒስቴር መስሪያ ቤቱ፣ ለተጠሪ ተቋማት፣ ለአጋር አካላት እና ለክልልና ለከተማ አስተዳደር የኮሙኒኬሽን ባለሙዎች የአቅም ግንባታ ስልጠና እየተሰጠ ይገኛል።
የአቅም ግንባታ ስልጠናው በዜና አጻጻፍ፣ በመልዕክት ቀረጻ፣ በማኅበራዊ ሚዲያ አጠቃቀምና ሞኒተሪንግ፣ በድረ ገጽ አጠቃቀምና የተቋማት ድረ ገጽ ትስስር እንዲሁም በአዲሱ የመገናኛ ብዙኃን አዋጅና የዲጂታል ሚዲያ አጠቃቀም ላይ ያተኮረ እና በተግባር ልምምድ የተደገፈ የአቅም ግንባታ ስልጠናው ይገኝበታል።
ስልጠናውን በንግግር የከፈቱት የባህልና ቱሪዝም ሚኒስትር የኮሚኒኬሽን ጉዳዮች ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር ዓለማየሁ ጌታቸው ባለሙያዎች ዘመኑን በዋጀ የድጅታል ሚዲያ በመጠቀም የመረጃ ልውውጡን ፈጣንና ቀልጣፋ ከማድረግ ውጭ አማራጭ የለም በማለት አስጀምረዋል፡፡