ኢንስቲትዩቱ እና የኢንተርፕሪነርሺፕ ልማት ኢንስቲትዩት በቅንጅት መስራት በሚቻልባቸው ጉዳዮች ዙሪያ ውይይት አካሄዱ፡፡

የቱሪዝም ማሰልጠኛ ኢንስቲትዩቱ እና የኢንተርፕሪነርሺፕ ልማት ኢንስቲትዩት የሥራ ኃላፊዎች በሥራ እድል ፈጠራ፣ ኢንተርፕራይዝ ስለማቋቋም፣ በአሰልጣኞች ስልጠና እና የተለያዩ የፈጠራ ሥራዎችን ለማዳበር በጋራ መስራት በሚቻልበት ሁኔታ ላይ ውይይት ማድረጋቸውን የማሰልጠኛ ኢንስቲትዩቱ ዋና ዳይሬክተር አቶ ጌታቸው ነጋሽ ገልጸዋል፡፡ ከነሐሴ ወር 2015 ዓ.ም ጀምሮ ሥራዎችን ለማከናወን የሚያስችሉ የበጀት ምንጮች ላይ ውይይት መደረጉንም ተናግረዋል፡፡
የሁለቱ ተቋም ተቀናጅቶ መስራት ለተቋም ባህል ግምባታ ከፍተኛ ጠቀሜታ እንዳለው የገለጹት የቱሪዝም ማሰልጠኛ ኢንስቲትዩት ምክትል ዋና ዳይሬክተር አቶ ገዛኸኝ አባተ ጠንካራ እንተርፕሪነር ለመፍጠር ሁኔታዎችን ለማመቻቸትም ያግዛል ብለዋል፡፡
የኢንተርፕሪነርሺፕ ልማት ኢንስቲትዩት ዋና ዳይሬክተር ዶክተር ሁሴን ሀሰን በበኩላቸው በቱሪዝም ዘርፍ እንተርፕሪነርን ለማስፋት በስልጠናና አስፈላጊ ጉዳዮች ከማሰልጠኛ ተቋሙ ጋር በቅንጅት ይሰራል ብለዋል፡፡