በማሰልጠኛ ኢንስቲትቱ የተጠኑ የባህል ምግቦችን ወደ ተግባር የማስገባትና አማራጭ ሜኑ ሆኖ እንዲቀርቡ እየተሰራ እንደሚገኝ ተገለጸ፡፡
ቱሪዝም ማሰልጠኛ ኢንስቲትዩት ያጠናቸውን የባህል ምግቦችን ወደ ተግባር የማስገባትና ደረጃቸውን በጠበቁ ሆቴሎች ውስጥ አማራጭ ሜኑ ሆኖ እንዲቀርቡ እየተሰራ እንደሚገኝ የኢንስቲትዩቱ ጥናት ምርምርና ማማከር ዘርፍ ም/ዋና ዳሬክተር አቶ ይታሰብ ሥዩም ገልጸዋል፡፡
ባለፈው ጊዜ ጥናት የተሰራባቸውን የባህል ምግቦች ሰነድን ለካፕታል ሆቴልና ስፓ ማስረከባቸውን የገለጹት አቶ ይታሰብ ሥዩም በዛሬው እለት የሲዳማ፣ ሀረሪ፣አፋርና የጋምቤላ ክልሎች እንዲሁም የጋሞ ባህላዊ ምግቦችን ለአንጋፋው ገነት ሆቴል በማስረከብ ሜኑ እየተዘጋጀላቸው መሆኑን ገልጸዋል፡፡
ለጊዜው ከሆቴሉ ደምበኞች ፍላጎት ጋር ሊሄዱ የሚችሉ ምግቦች ላይ ትኩረት መደረጉን የገለጹት ም/ዋና ዳይሬክተሩ እነዚህ ምግቦች የደምበኞችን ፍላጎት ሊያረኩ የሚችሉ ናቸው ብለዋል፡፡
የገነት ሆቴል ዋና ሼፍ ግርማ ዝቃርጌ በበኩላቸው ምግቦችን አዘጋጅቶ ለገበያ ለማቅረብ ተጨማሪ ወጪ ወጥቶባቸው ከውጭ ተገዝተው ከሚቀርቡ ይልቅ የባህል ምግቦችን አዘጋጅቶ በማቅረብ ውጤታማ መሆን ይቻላል ብለዋል፡፡
ለሙከራ ለደምበኞች ከቀረቡ ምግቦች ጥሩ ግብረ መልስ መገኘቱን የገለጹት ሼፉ በባህል ምግቦች ውስጥ የሚገኙትን ግብዓቶች በጠቀም የተሻለ ሜኑ ማዘጋጀትም ይቻላል ብለዋል፡፡
ትክክለኛ የተቋሙን መረጃዎች ለማግኘት የሚከተሉትን ማስፈንጠሪያዎችን ይጠቀሙ
ፌስቡክ፡ https://www.facebook.com/tticommunication
ቴሌግራም ፡https://t.me/tticommunication
ዌብሳይት፡ https://www.tti.edu.et/
Recent Comments