የ ‘’ነጩ ፖስታ ጎርፍ ወደ ነጩ ቤተመንግስት ሀገራዊ ንቅናቄ በባህልና ቱሪዝም ሚኒስቴር ተከናወነ፡፡

አዲስ አበባ የባህልና ቱሪዝም ሚኒስቴር እና የተጠሪ ተቋማት አመራሮችና ሠራተኞች የ ‘’ነጩ ፖስታ ጎርፍ ወደ ነጩ ቤተመንግስት’’ በሚል ሃሳብ በሃገር አቀፍ ደረጃ የተጀመረዉን ንቅናቄ ተቀላቅሏል፡፡
ዘመቻዉን ያስጀመሩት የባህልና ቱሪዝም ሚኒስቴር ሚኒስትር ዶክተር ሂሩት ካሳዉ ሲሁኑ ወቅት ሃገራችን በጦርነት ዉጊያ ብቻ ሳይሆን በኢኮኖሚያዊ እንዲሁም በማህበራዊ ሚዲያዎች ፈተና እንደገጠማት ገልፀዉ ይህ ዘመቻ በግንባር ብቻ ሳይሆን ከቢሮ ዉስጥ ሆነን ዋናዉን የልማት ሥራዎች እየሰራን በአለም ላይ የዲፕሎማሲያዊ ደጀንነት ሥራ በመስራት እዉነት ኮስሶ ዉሸት የነገሰበትን ፕሮፖጋንዳ በማፈራረስ በመላዉ ዓለም የዳግማዊ አድዋ ታሪክ ሠሪዎች ለመሆንና የኢትዮጵያን እውነት በነጩ ፖስታ ለዓለም በማሰረዳት የሃገራችንን ሉአላዊነት ማስጠበቅ የምንችልበት ዘመቻ ነዉ ብለዋል፡፡