ቱሪዝም ማሰልጠኛ ኢንስቲትዩት ከስልጤ ዞን ጋር በመተባበር የዓለም ቱሪዝም ቀንን እያከበረ ነው።

ቱሪዝም ማሰልጠኛ ኢንስቲትዩት ከስልጤ ዞን ጋር በመተባበር የዓለም ቱሪዝም ቀንን በተለያዩ ዝግጅቶች ለማክበር አሁን የመክፈቻ ፕሮግራም እና የውይይት መነሻ የሚሆን ሶስት የጥናት ጽሑፎች ይቀርባሉ ።
በመክፈቻ ፕሮግራሙ የሥራና ክህሎት ሚኒስቴር ዴኤታ ዶ/ር ተሻለ በሬቻ እንደገለጹት የዓለም የቱሪዝም ቀን በሀገራችን ለ36ኛ ጊዜ “ቱሪዝም ለአረንጓዴ ልማት፤ አረንጓዴ ልማት ለቱሪዝም” በሚከበረው በዓል ያለንን ዕምቅ የቱሪዝም ሀብቶች መጠቀም የሚያስችል የጥናትና ምርምር ሥራ መሥራትና ሀገርን ተጠቃሚ ማድረግ እንደሚገባ ኢንስቲትዩቱ በዚህ ዘርፍ ከስልጤ ዞን ጋር በመተባበር ማዘጋጀቱን አመስግነዋል።
የኢንስቲትዩቱ ዋና ዳይሬክተር አቶ ጌታቸው ነጋሽ በበኩላቸው ቱሪዝም የኢኮኖሚ እና ማህበራዊ ግኑኝነትን ማጠናከር የሚችል ዘርፍ በመሆኑ አሁን በስልጤ ዞን የተሰራው ሥራ ወደ ሌሎች ክልሎችና ዞኖች ማስፋትና ማዳረስ መቻል አለብን ብለዋል።
በነገው ዕለትም ማሰልጠኛ ኢንስቲትዩቱ የዞኑን የቱሪዝም ሃብቶች እና መዳረሻዎችን እንዲሁም 18 የሚሆኑ ባህላዊ ምግቦች በሜኑ መልክ አዘጋጅቶ ማቅረብ የሚያስችል ጥናትም በባለሙያዎቹ አስጠንቶ ለዞኑ የሚያስረክብ ይሆናል።
ቱሪዝም ማሰልጠኛ ኢንስቲትዩት ማሰልጠን፣ ማማከር እና ምርምር ማድረግ የሚሉ ሶስት አንኳር ተልዕኮዎችን የሚያስፈጽም መንግስታዊ ተቋም ነው።
መስከረም 19/2016 ዓ.ም
ትክክለኛ መረጃ ለማግኘት የሚከተሉትን ሊንክ በመጠቀም የፌስቡክ ገጻችንይጎብኙ፣ ላይክ፣ ሼር ያድርጉ