“ኢትዮጵያ በዱር እንስሳትና ዕጽዋት (flora and fauna) ሀብት ስማቸው ከሚጠቀሱ ሀገራት መካከል በቀዳሚነትጠቀሳለች።” አቶ ተከተል አጥናፉ የተፈጥሮ ባለሙያ።

ኢትዮጵያ በዱር እንስሳትና ዕጽዋት (flora and fauna) ሀብት ስማቸው ከሚጠቀሱ ሀገራት መካከል በቀዳሚነት የምትጠቀስ መሆኗን የተፈጥሮ ባለሙያና አማካሪ አቶ ተከተል አጥናፉ ገለጹ።
አቶ ተከተል ሀገራችን ያላትን የተፈጥሮ ሀብት በሚገባ ልክ ለማስተዋወቅና በማስጎብኘት ከቱሪዝም ከዘርፍ የሚገውን ጥቅም ለማግኘት የሰለጠነና ብቃት ያለው የሰው ሀይል ያስፈልጋል ብለዋል።
ይህን ኃላፊነት ለመወጣት የስልጠናውን ተደራሽነት ለማስፋት በዘርፉ ላይ ስልጠና እየሰጡ ለሚገኙ መምህራን በማሰልጠኛ ኢንስቲትዩቱ ባለሙያዎችና እንዱስትሪው ውስጥ ባሉ ሙያተኞች እየተሰጠ ይገኛል።
ከመስከረም 05/2016 ዓ.ም ጀምሮ እየተካሄደ ባለው የአቅም ግምባታ ስልጠና ለቱሪዝም አሰልጣኞች የንድፈሃሳብና የተግባር ተኮር ስልጠና በቢሾፍቱ በሚገኙ ሀይቆችና አካባቢው በአቶ ተከተል አጥናፉ ተሰጥቷል።
ውድ የገጻችን ተከታዮች ላይክና ሼር በማድረግ መረጃዎችን ተደራሽ እንድታደርጉልን እንጠይቃለን ።