ግንቦት 12/2017 ዓ.ም
ቱሪዝም ማሰልጠኛ ኢንስቲትዩት ከሊድ ዋይስ ጋር በሊደርሺፕ ሥልጠና ፣ በማማከርና በተመራቂዎች ሥራ ዕድል ፈጠራ ላይ አብሮ ለመስራት የጋራ ስምምነት ተፈራረሙ፡፡ቱሪዝም ማሰልጠኛ ኢንስቲትዩት ዋና ዳይሬክተር አቶ ጌታቸው ነጋሽ የሚደረገው የጋራ ስምምነት በልምድ የተገኙ የሆቴልና ቱሪዝም ሙያዎችና እውቀትን ወደ ደረጃ (ስታንዳርድ) ለማምጣት፣ በጥናትና ምርምር እንዲሁም በሊደርሺፕ ስልጠና በጋራ ለመስራት የሚያግዝ መሆኑን ገለጸው እቅዶችን በማዘጋጀት ወደ ተግባር መቀየር ይገባል ብለዋል፡፡

የሊድ ዋይስ መስራችና ማናጀር አቶ መልካሙ መኮንን ሊድ ዋይስ ተመራቂ ተማሪዎችን ወደ ሥራ በማሰማራት፣ በሆስፒታሊቲ እንዱስትሪ ውስጥ የተሻለ አገልግሎት ለመስጠት እንቻል ተሰጥኦን መሰረት ያደረገ የስራ ስምሪት እንዲኖር ስልጠናዎችን የሚሰጥ መሆኑን ጠቅሰው ከኢንስቲትዩቱ ጋር በዘርፉ ውስጥ የተሻለ አገልግሎት ለመስጠት በሚያስችሉ ጉዳዮች ላይ አብረን እንሰራለን ብለዋል፡፡
ትክክለኛ መረጃዎችን ለማግኘት የሚከተሉትን ማስፈንጠሪያዎችን ይጠቀሙ
ፌስቡክ፡ https://www.facebook.com/tticommunication
ቴሌግራም ፡https://t.me/tticommunication
ዌብሳይት፡ https://www.tti.edu.et