ቱ.ማ.ኢ ነሐሴ 15/2017 ዓ.ም ቱሪዝም ማሰልጠኛ ኢንስቲትዩት በስልጠና ፣በጥናትና ምርምር እንዲሁም በቦንጋ ከተማ የሚገኙትን ሆቴሎች አቅም ለመገንባት የሚያስችል የጋራ ስምምነት ተፈራርመዋል፡፡ ማሰልጠኛ ኢንስቲትዩቱ በሀገር አቀፍ ደረጃ በሆቴልና ቱሪዝም ሙያዎች ስልጠና ከሚሰጡ ኮሌጆች ጋር የአሰልጣኞች ስልጠና በመስጠት ፣
በአካባቢው የሚገኙ የሆቴልና ቱሪዝም ተቋማትን ለማጠናከር እየሰራ መሆኑን የገለጹት የኢንስቲትዩቱ የስልጠናና ተቋማት አቅም ግንባታ ም/ዋና ዳይሬክተር አቶ ሀብታሙ ክብረት ገልጸዋል።ኢንስቲትዩቱ ከተለያዩ ፖሊቴክኒክ ኮሌጅ ለተወጣጡ የሆቴል ዘርፍ መምህራን የአጭር ጊዜ ስልጠና እየሰጠ የሚገኝ ሲሆን የቦንጋ ፖሊቴክኒክ ኮሌጅም በስልጠናው ላይ እየተሰተፉ ይገኛሉ፡፡
የጋራ ስምምነት ፊርማው ነሐሴ 06/2017 ዓ.ም በማሰልጠኛ ኢንስቲትዩቱ ተከናውኗል፡፡
ትክክለኛ መረጃዎችን ለማግኘት የሚከተሉትን ማስፈንጠሪያዎችን ይጠቀሙ
ፌስቡክ፡ https://www.facebook.com/tticommunication
ቴሌግራም ፡https://t.me/tticommunication
ዌብሳይት፡ https://www.tti.edu.et


Recent Comments