ቱ.ማ.ኢ ጥር 22/2017 ዓ.ም
ቱሪዝም ማሰልጠኛ ኢንስቲትዩት ለአንድ ዓመት ሲያካሂድ የነበረውን የዝግጅት ምዕራፍ እያጠናቀቀ መሆኑን የኢንስቲትዩቱ ዋና ዳይሬክተር አቶ ጌታቸው ነጋሽ ገልጸዋል ።
በሀገር አቀፍ ደረጃ የመንግስት አገልግሎት አሰጣጥን ለማሻሻል እየተሰራ የሚገኘውን የሪፎርም ስራ ተከትሎ ከተመረጡ ተቋማት መካከል ቱሪዝም ማሰልጠኛ ኢንስቲትዩት አንዱ መሆኑን የገለጹት ዋና ዳይሬክተሩ ለባለፈው አንድ ዓመት የተለያዩ ኮሚቴዎችን በማቋቋም ከሰነድ ዝግጅት ባለፈ ተቋሙን ለለሠራተኛው እና ለሥራ ምቹ ማድረ ላይ ሰፊ ሥራ መሰራቱን ፣ የአገልግሎት አሰጣጣችንን ውጤታማ ለማድረግ የሚያስችሉ በርካታ ሥራዎች ወደ ተግባር መገባታቸውን እና ሪፎርሙን አስመለክቶ የሰራተኞች ውይይት መደረጋቸውን ገልጸዋል።
በተጨማሪም ይህ ሪፎርም የመንግስት አገልግሎትን በዲጅታል ለመስጠት ከታቀደው ጋርም የሚገናኝ ሲሆን እንደ ማሰልጠኛ ኢንስቲትዩቱ ሁሉም ሠራተኛ ዲጂታል መታወቂያ እንዲኖረው ማድረግ የኢንፎርሜሽን ኮሚንኬሽን መሠረተ ልማት ማዕቀፍ ሥራዎች ወደ ተግባር ምዕራፍ ለመግባት የሚያስችል ነው ብለዋል ።
በዚህ የቱሪዝም ማሰልጠኛ ኢንስቲትዩት የሰራተኞች ብቃት ማዕቀፍ ውይይት መድረክ ላይ ሰነድ ያቀረቡት የኢንስቲትዩቱ የስልጠናና ተቋማት አቅም ግንባታ ዘርፍ ም/ዋና ዳይሬክተር አቶ ሀብታሙ ክብረት የተቋሙን አገልግሎት ለማሻሻል የሰራተኞች የሙያ ብቃት ፣ ክህሎትና ለስራው የሚያስፈልግ ባህሪ መላበስ ይገባል ብለዋል። ይህን ለማረጋገጥ ያለውን የምዘና ስርዓት ለሰራተኞች ማብራሪያ ተሰጥቷል።
ሌሎች ንዑሳን ኮሚቴዎች የሠሯቸውን ሰነዶች ቀርበው ውይይት ተደርጎላቸዋል።
Recent Comments