ቱ.ማ.ኢ የካቲት 08/2017 ዓ.ም ቱሪዝም ማሰልጠኛ ኢንስቲትዩት በአቃቂ ቃሊቲ ክፍለ ከተማ ወረዳ 12 በEASTRIP ፕሮጀክት አማካኝነት የልህቀት ማዕከል ለመገንባት እየተሰራ በሚገኘው ግንባታ ዙሪያ ከወረዳው ነዋሪ ተወካዮች ጋር ውይይት አካሂደዋል ።
በመድረኩ የመክፈቻ ንግግር ያደረጉት የኢንስቲትዩቱ ዋና ዳይሬክተር አቶ ጌታቸው ነጋሽ አንድ ፕሮጀክት ሲገነባ ለአካባቢው ህብረተሰብ የሚሰጠው ጠቀሜታ የስልጠና፣ የሥራ ዕድል እና ሌሎች የማህበረሰብ አቀፍ አገልግሎቶችን ተጠቃሚ የሚያደርግ ዘርፈ ብዙ አገልግሎቶችን ይዞ እንደሚመጣ ገልጸው፤ ማሰልጠኛው የሚገነባው የቱሪዝም የልህቀት ማዕከል በሀገር አቀፍ ደረጃ ልዩ ትኩረት የተሰጠው በመሆኑ የአካባቢው ነዋሪም በዚህ ተጠቃሚ ስለሚሆን ለፕሮጀክቱ መሳካት የበኩሉን ድጋፍ እና ትብብር እንዲያደርግ በመልእክታቸው ገልጸዋል።
የተቋሙ EASTRIP ፕሮጀክት አስተባባሪ አቶ አብርሃም ለገሰ እንደገለጹት ይህ ፕሮጀክት ወደ አካባቢ በመሄዱ በቀጥታም ሆነ በተዘዋዋሪ የማይጠቀም የማህበረሰብ ክፍል እንደማይኖር ገልጸው። ይህም ተቋሙ በቱሪዝምና በሆቴል ዘርፍ በመደበኛ በቀንና በማታ በቅዳሜና እሁድ በአጫጭር እና ረዥም ስልጠናዎችንና ምርምርና ማማከር እንዲሁም በርካታ ማህበረሰብ አቀፍ አገልግሎቶችን የሚሰጥ በመሆኑ ጠቀሜታው የጎላ ይሆናል ብለዋል።
ከውይይቱ ተሳታፊዎች ወ/ሮ ሳይደያ ከይረዲን እንደተናገሩት ይህ ትልቅ ተቋም ወደ ወረዳችን መምጣቱ ትልቅ እድል ነው በማለት ተቋሙ ሀገር አቀፍ በመሆኑ ምንም አይነት ልዩነት ሳይኖር እንድንጠቀም ይረዳናል ብለዋል።
አቶ ፍቅሩ ዳኛው እና አቶ አብርሃም ዲቢንቶ ሌሎች የውይይቱ ተሳታፊዎች ሲሆኑ ፕሮጀክቱ ወደ አከባቢያችን መምጣቱን እንደ ትልቅ ጸጋ እናየዋለን በማለት ከአካባቢው ማህበረሰብ የሚጠበቀውን ሁሉ አብሮ ለመስራትና ወክለው የመጡትን ነዋሪ ስለተቋሙ ለማሳወቅ ፍቃደኞች መሆናቸውን ገልጸዋል የማሰልጠኛ ኢንስቲትዩቱንም ጎብኝተዋል።
የግንባታ ቦታው አቃቂ ቃሊቲ ክፍለከተማ ወረዳ 12 መሆኑ ከዚሀ ቀደም መጥቀሳችን ይታወቃል ።
ትክክለኛ መረጃዎችን ለማግኘት የሚከተሉትን ማስፈንጠሪያዎችን ይጠቀሙ
ፌስቡክ፡ https://www.facebook.com/tticommunication
ቴሌግራም ፡https://t.me/tticommunication
ዌብሳይት፡ https://www.tti.edu.et

Recent Comments