ማስልጠኛ ኢንስቲትዩቱና የአውስትሪያ አምባሲ አብሮ ለመስራት በሚቻልባቸው ጉዳዮች ዙሪያ ውይይት አካሄዱ።
ቱ.ማ.ኢ ሐምሌ 12 / 2016 ዓ.ም
ቱሪዝም ማሰልጠኛ ኢንስቲትዩትና የአውስትሪያ አምባሲ በቱሪዝም ዘርፍ አብሮ ለመስራት በሚቻልባቸው ጉዳዮች ላይ የኢንስቲትዩቱ ኃላፊዎችና አምባሳደር ሲሞኔ ናፕ ውይይት አካሂዷል።
ሀገራችን ከፍተኛ የቱሪዝም ሀብት ያላት በመሆኑ የማሰልጠኛ ተቋሙ ለዘርፉ የሚሆን የሰለጠነ የሰው ሀይል በማቅረብ፣ የተለያዩ ጥናትና ምርምሮች እንደሁም የማማከር አገልገሎትን እየሰጠ እንደሚገኝ ማብራሪያ የሰጡት የኢንስቲትዩቱ የምርምርና ማማከር ዘርፍ ም/ዋና ዳይሬክተር አቶ ይታሰብ ስዩም በአቅም ግንባታ፣ ኢንዱስትሪው ተለዋዋጭ ባህሪ አንጻር በልምድ ልውውጥ እና በመሰረተ ልማት ዘርፍ በዘላቂነት ከአንባሲው ጋር ለመስራት ፍላጎት እንዳለ ገልጸዋል፡፡
መንግስት ለቱሪዝም ዘርፍ ከፍተኛ ትኩረት ሰጥቶ እየሰራ መሆኑን የገለጹት የኢንስቲትዩቱ አስተዳደርና ሥራ አመራርና ዘርፍ ም/ዋና ዳይሬክተር አቶ ገዛኸኝ አባተ ከኢምባሲው እና እንደ ሀገርም የቱሪዝም ዘርፉን ለማሳደግ በዘላቂነት በትብብር አብሮ መስራት ይቻላል ብለዋል፡፡
የአውስትሪያ አምባሳደር ሲሞኔ ናፕ በበኩላቸው ሀገራቸው ከአውሮፓ ሀገሮች በቱሪዝም ገቢ ሁለተኛ ደረጃ ላይ የምትገኝ መሆኗን ገልጸው የኢትዮጵያ መንግስት ለቱሪዝም ዘርፍ የሰጠውን ትኩረት አድንቀዋል፡፡ ቱሪዝም እንደ ሀገርም ሆነ በቀጠናው በጣም አስፈላጊ የኢኮኖሚ መስክ ሆኖ እንዲቀጥል ትኩረት ሊሰጠው ይገባል ብለዋል፡፡ ኢምባሲው ከተለያዩ የሀገራችን ዩኒቨርሲቲዎች ጋር በትብብር እየሰራ እንደሚገኝ የገለጹት አምባሳደር ሲሞን ናፕ ከቱሪዝም ማሰልጠኛ ኢንስቲትዩት ጋር በሚበቀጣይነት በትብብር እንደሚሰራ ገልጸዋል።
ትክክለኛ የተቋሙን መረጃዎችን ለማግኘት የሚከተሉትን ማስፈንጠሪያዎችን ይጠቀሙ
ፌስቡክ፡ https://www.facebook.com/tticommunication
ቴሌግራም ፡https://t.me/tticommunication
ዌብሳይት፡ https://www.tti.edu.et/
Recent Comments