የኮሮናቫይረስ ጀርሞች ኮሮናቨረዴ የሚባል ፋሚሊ ዉስጥ የሚካተቱ ናቸው፡፡ እነዚህም እንስሳትንና ሰዎችን ያጠቃሉ ወይም ያሳምማሉ፡፡
ሰውን የሚያጠቃው ኮሮናቫይረስ ቀላል ከሆነ በሽታ ለምሳሌ እንደጉንፋን አይነት እስከ አደገኛ የሆነ ህመም ሊያመጣ የሚችል በሽታ ያመጣሉ፡፡
ጥቂት የኮሮኖቫይረስ ዝርያዎች በእንስሳት ላይ በሽታ የሚያመጡ ሰዎችንም የሚያጠቁ አሉ፡፡ እነዚህም zoonotic diseases ይባላሉ፡፡
ኮሮና ቫይረስ በ 1960 ተገኘ
COVID-19 ታህሳስ 21 በ ቻይና ዉሃን ግዛት ተገኘ
SARS, MERS ወረርሽኞች 2003፣ 2012 ተከስተው ነበር
“COVID-19 ለምን አሳሳቢ ሆነ?”
******************************
– ከዚህ በፊት ሰዉን ይዞ ስለማያዉቅ ሰዎች በተፈጥሮ ከየሚያዳብሩት – —
– መከላከያ ስለሌላቸዉ
– የከፋ ደረጃ ከደረሰ ሞት ሊያስከትል ስለሚችል
– ክትባት ስለሌለዉ
– ምልክቶችን ማስታገስ እንጂ እስካሁን ምንም መዳኒት ስለሌለዉ
– በጣም በፍጥነት ስለሚተላለፍ
“የኮሮናቫይረስ በሽታ መተላለፊያ መንገዶች”
***************************************
የ COVID-19 በሽታ ከሰው ወደ ሰው የሚታላለፈው አብዛኛውን ጊዜ በሳልና በማስነጠስ ጊዜ ከአፍና አፍንጫ በሚወጡ ረቂቅ የፈሳሽ ጠብታዎች ወይም ብናኞችን በምንተነፍስበት ጊዜ ወደ ሰዉነታችን ካስገባን
በበሽታዉ ከተያዘ ሰዉ ንክኪ ከፈጠሩ በህዋላ (ምሳሌ- እጅ ለእጅ በመጨባበጥ) ባልታጠበ እጅ አፍን አፍንጫን እና አይንን በመነካካት
በበሽታዉ ከተያዘ ሰዉ በሚወጡ የአፍ እና የአፍንጫ ፈሳሾች የተበከሉ ፣ እቃዎች እና ወለሎች ጋር ንክኪ አድርጎ ባልታጠበ እጅ አፍን አፍንጫን እና አይንን በመነካካት
በሽታው በአገራችን የሌለ በመሆኑ ከእንስሳት ተዋጽኦ ምግቦች ጋር የሚመጣ የበሽታው ስርጭት ወይም የመጋለጥ ስጋት የለም፡፡
“የበሽታው ምልክቶች”
*******************
የበሽታው ምልክቶች፡-
– ትኩሳት
– ማሳል
– የትንፋሽ ማጠር
– ለመተንፈስ መቸገር
በሽታው እየተባባሰ ሲሄድም፡-
– የሳምባ ምች
– የኩላሊት ስራ ማቆምና ሞት ያስከትላል፡፡
“መከላከያ መንገዶች”
*******************
እጅን በአልኮል የተዘጋጀ መታሻ ወይም በሳሙና አዘዉትረዉ መታጠብ
እጆትን ሳይታጠቡ አይንን፣ አፍን ና አፍንጫን አለመንካት
በሚያስልም ሆነ በሚያስነጥስ ጊዜ አፍንና አፍንጫን በመሀረብ ወይም በሶፍት ወይም በክንድን በአፍና አፍንጫን መሸፈን
የተጠቀሙበትን ሶፍት ወረቀትና ተመሳሳይ ነገር ወዲያውኑ በሚከደን ቆሻሻ ማጠራቀሚያ ዉስጥ መጣል
የመጨባበጥ ሰላምታን ማቆም
በየጊዜው ከጤና ጥበቃ/የኢትዮጵያ ህብረተሰብ ጤና ኢንስቲትዩት ስለበሽታው ሁኔታ የሚወጡ መረጃዎችን መከታተልና ተግባራዊ ማድረግ
ምንጭ፡- የኢትዮፕያ ህብረተሰብ ጤና ኢንስቲቲዉት, ጤና ሚኒስቴር –
ኢትዮጲያ
Recent Comments