የሥራና ክህሎት ሚኒስቴር ከቱሪዝም ማሰልጠኛ ኢኒስቲትዩት ጋር በመተባበር 25 ዝቅተኛ ደሞዝ ተከፋይ ሴት ሰራተኞችን በምግብ ዝግጅት አሰለጠነ።

በስልጠናው ማጠቃለያ ላይ የቱሪዝም ኢኒስቲትዩት ም/ዋና ዳይሬክተር አቶ ሀብታሙ ክብረት ባስተላለፉት መልዕክት የምግብ ዝግጅት በአሁኑ ጊዜ እጅግ ተፈላጊ ሙያ በመሆኑ ሰልጣኞቸ የራሳቸውን የፈጠራ በመጠቀም ተጨማሪ ገቢ ማመንጨት የሚችሉበት አቅም ተፈጥሮላቸዋል ብለዋል።
ሰልጣኞች በቀጣይ የራሳቸዉን ስራ ለመፍጠር የሚያደርጉትን ጥረት ለማገዝ ኢኒስቲቲዩት ዝግጁ መሆኑንም ተናግረዋል ።
ስልጠናውን ያስተባበረው በሥራና ክህሎት ሚኒስቴር የሴቶችና ማህበራዊ ጉዳዮች አካቶ ትግበራ ስራ አስፈጻሚ ወ/ሮ እርቅነሽ ዮሀንስ እንደገለፁት ስልጠናው ሚኒስቴር መ/ቤቱ ዝቅተኛ ደመወዝ ተከፋይ ሴት ሰራተኞችን ህይወት ለማሻሻል በትኩረት ከሚተገብራቸው ዕቅዶች መካከል አንዱ ነው።
በቀጣይም በትምህርትና ስልጠና ሴቶችን ለማብቃት የሚደረገው ጥረት ተጠናክሮ እንደሚቀጥል ተናግረዋል ።
ሰኔ 24/2015 ዓ.ም፡ የሥራና ክህሎት ሚኒስቴር፡
ለወቅታዊ ትኩስ የሥራና መረጃዎች
ቴሌግራም፦https://t.me/fdre_mols በመወዳጀት ይከታተሉን::