ግንቦት 3/2015 ዓ.ም
ቱሪዝም ማሰልጠኛ ኢንስቲትዩት ማክሰኞ ግንቦት 8/2015 ዓ.ም በሚካሄደው የመስተንግዶና የክህሎት ሳምንት ለተመራቂ ሰልጣኞች በተለያዩ ርዕሶች ለሥራ የሚያዘጋጅ ስልጠና ተሰጥቷል፡፡

ስልጠናውን የሰጡት ከአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ ዶ/ር ብርሃኑ አማረ ሲሆኑ ስልጠናዎቹ በሲቪ አዘገጃጀት፣ የሥራ ቃለ መጠይቅ እና ሥራ ለማግኝት የሚያስፈልጉ ቅድመ ዝግጅቶችን በተመለከተ የግንዛቤ ማስጨበጫ ተካሂዷል፡፡
ይህ ስልጠና የመስተንግዶና የክህሎት ሳምንት ፕሮግራሞች አንዱ ቀጣሪንና ባለሙያዎችን የሚያገናኘው Job Fair ፕሮግራም አንዱ ነው፡፡
በዚህ መድረክ ቀጣሪ ሆቴሎችና አስጎብኝ ድርጅቶች ይገኛሉ፤ የተቋሙ እጩ ሰልጣኞችና ከዚህ ቀደም ሥራ ላይ ያልነበሩ ሰልጣኞችም ተገኝተው ራሳቸውን ከቀጣሪዎች ጋር የሚያገናኙበት ትልቅ መድረክ ነው ሲሉ የፕሮግራሙ አስተባባሪ አቶ ሄኖክ መሀሪ ገልጸዋል፡፡