ሆ.ቱ.ሥ.ማ.ኢ መስከረም 19/2012 ዓ.ም
የባህል ቱሪዝምና ስፖርት ሚኒሰቴር እና የድሬ ዳዋ ከተማ አስተዳደር በጋራ በመሆን ቱሪዝም ለስራ እድል ፈጠራና ለተሻለ ህይወት! በሚል መሪቃል በሀገራችን 32ኛው ዓለም አቀፍ የቱሪዝም ቀን ምክንያት በማድረግ በድሬዳዋ ከተማ የ40 ኪሎሜትር ልዩ የብስክሌት ውድድር የባህል ቱሪዝምና ስፖርት ሚኒስቴርና የከተማ አስተዳደሩ ከፍተኛ የስራ ኃላፊዎች እንዲሁም ተጋባዥ እንግዶች በተገኙበት ተካሂዷል ።
በብስክሌት ውድድሩ አሚር ጃፋር 1ኛ፣ ተስቲ ዮሱፍ 2ኛ እና 3ኛ አክረም ከድር በመውጣት ያጠናቀቁ ሲሆን እጅግ ከፍተኛ ፉክክር የተደረገበት ነበር።
ለአሸናፊዎችም የገንዘብና የምስክር ወረቀት ተበርክቶላቸዋል።