ቱማኢ ታህሳስ 1/2018 ዓምቱሪዝም ማሰልጠኛ ኢንስቲትዩት በልደታ ክ/ ከተማ ውስጥ ለሚገኙ ከየተለያዩ ወረዳዎች ለተውጣጡ ወጣት ሥራ ፈላጊ ሴቶች በሆቴል እና ቱሪዝም ዘርፍ ግንዛቤ ማስጨበጫ ስልጠና ሰጠ፡፡ ስልጠናው ወጣቶቹ ስለ ሆቴልና የቱሪዝም ሙያ ግንዛቤ ኖሯቸው በመስኩ ለመሰማራትና ሥራ ለመፍጠር ፍላጎት ካላቸው ከወረዳዎቹ ጋር
በመተባበር በኢንተርፕራይዝ ተደራጅተው ውጤታማ እንዲሆኑ ለማስቻልና አስፈላጊውን ድጋፍ እና በዘርፋ የማማከር አገልግሎት ለማድረግ ታሳቢ ያደረገ መሆኑን የተቋሙ የማማከርና ማርኬቲንግ ዴስክ ኃላፊ አቶ ታምራት ተፈራ ገልፀዋል፡፡
ኢንስቲትዩቱ በቱሪዝምና ሆቴል ሙያዎች ከማሰልጠን እና የምርምር ሥራዎች ከማድረግ ባሻገር በማህበረሰብ አቀፍ አገልግሎት ዜጎች ሥራ ፈጣሪ ሆነው በግል ወይም በቡድን ተደራጅተው ራሳቸውን እንዲችሉ የማድረግ ሥራዎችን ሲሰራ መቆየቱንም ገልፀዋል፡፡
ስልጠናውን በዘርፉ የካበተ ልምድ ያዳበሩት የኢንስቲትዩቱ አሰልጣኞች አሰልጣኝ አብይ ከበደ እና አሰልጣኝ አብይ ንጉሴ ሰጥተዋል፡፡
የቱሪዝም ዘርፍ በዓለም ላይ ለዜጎች የሥራ ዕድል በመፍጠር ከሚታወቁ ዘርፎች በተለይም ወጣቶችና ሴቶችን ተጠቃሚ የሚያደርግ መሆኑ ይጠቀሳል፡፡
ትክክለኛ መረጃዎችን ለማግኘት የሚከተሉትን ማስፈንጠሪያዎች ይጠቀሙ
ፌስቡክ፡ https://www.facebook.com/tticommunication
ቴሌግራም ፡https://t.me/tticommunication
ዌብሳይት፡ https://www.tti.edu.et/


Recent Comments