ቱ.ማ.ኢ መጋቢት 21/2015 ዓ.ምየሥራና ክህሎት ሚኒስቴር ከቱሪዝም ሚኒስቴርና ከቱሪዝም ማሰልጠኛ ኢንስቲትዩት ጋር
በመተባበር በሆቴል ሙያ ማህበራት ስለ ሙያ ደህንነትና ጤንነት አጠባበቅ ዙሪያ የግንዛቤ ማስጨበጫ ስልጠና ተሰጠ፡፡
ስልጠናውን በንግግር የከፈቱት የቱሪዝም ማሰልጠኛ ኢንቲትዩት ዋና ዳይሬክተር ክቡር አቶ ጌታቸው ነጋሽ በመልዕክታቸው እንደገለጹት አገራችን ከተቀበለቻቸው ዓለም አቀፍ ህጎች የሥራ ላይ ደህንነት እና ጤንነት ከቀዳሚዎቹ አንዱ ነው፤ አሰሪ ለሰራተኛው ምቹ የሥራ አካባቢ ማመቻቸትና ከአካላዊና ኬሚካላዊ ጉዳት የመጠበቅ ግዴታ አለበት ብለዋል።
በቱሪዝምና ሆስፒታሊቲ ኢንደስትሪ የሰራተኛው ብቻ ሳይሆን የደንበኛንም ደህንነት እንደምሳሌ መጠበቅ በምግብና መጠጥ ዝግጅት የመሳሰሉት ወሳኝ መሆናቸውን ጠቅሰዋል፡፡
ዋና ዳይሬክተሩ አገልግሎታችን ዓለም አቀፍ ደረጃውን የጠበቀ እንዲሆን እና የደንበኞቻችንንም ሆነ የሰራተኞቻችን ደህንነትና ጤንነት መጠበቅ ይጠበቅብናል፤ ለዚህም እዚህ ስልጠና ላይ የተሳተፋችሁ የሙያ ማህበራት ሃላፊነታችሁን ለመወጣት በስልጠናው ስለተገኛችሁ እናመሰግናለን ብለዋል፡፡
ስልጠናውን የሰጡት ከሥራና ክህሎት ሚኒስቴር አቶ አብነት ፍቃዱ ናቸው።
አቶ አብነት የሙያ ደህንነት ከሚያስፈልጋቸው ዘጠኝ የኢንደስትሪ ዘርፎች አንዱ የቱሪዝምና ሆስፒታሊቲ መሆኑን ጠቅሰው ነገር ግን በዘርፉ የደህንነትና ጤንነት ግንዛቤው አናሳ መሆኑን አንስተዋል።
ይህ ስልጠና ለዘርፉ ባለሙያዎች እንዲሰጥ ያስተባበሩትን ሁለቱን ሚኒስቴር መ/ቤቶችና ኢኒስቲቲዩቱን አመስግነዋል።
ኢትዮጵያ የዓለም አቀፉ የሥራ ላይ ደህንነት ህግ የተቀበለችው ከ1923ዓ.ም ጀምሮ መሆኑ በስልጠናው ተጠቅሷል።
Recent Comments