ቱ.ማ.ኢ ጥር 22/2017 ዓ.ም
ቱሪዝም ማሰልጠኛ ኢንስቲትዩት እና አዲስ አበባ ዩኒቨርስቲ በሀገራችን የመጀመሪያ የሆነውን የኢንግሊዘኛ አማርኛ የቱሪዝም መዝገበ ቃላት ለማዘጋጀት ተፈራርመዋል ።
የኢንስቲትዩቱ ዋና ዳይሬክተር አቶ ጌታቸው ነጋሽ ሁለቱ አንጋፋ ተቋማት በጋራ ለመስራት ማሰልጠኛ ኢንስቲትዩቱ መዝገበ ቃላቱን ለማዘጋጀት ተነሳሽነት በመውሰድ፣ ይህን ለትውልድ የሚጠቅም ሥራ ከዩኒቨርስቲው ጋር በመሆን ያጠናቅቃል ብለዋል።
ኢንስቲትዩቱ ለረጅም ዓመታት በስልጠና ፣ በጥናትና ምርምር እና ማህበረሰብ አቀፍ አገልግሎት ለዘርፋ እድገት የበኩሉን ከፍተኛ አስተዋጽኦ ያደረገ መሆኑን ያስታወሱት ዋና ዳይሬክተሩ ከመዝገበ ቃላት ዝግጅት ባለፈም ከአዲስ አበባ ዩኒቨርስቲ ጋር በቀጣይነት እንሰራለን ብለዋል።
የአዲስ አበባ ዩኒቨርስቲ ተጠባባቂ ፕሬዝዳንት ዶ/ር ሳሙኤል ክፍሌ በበኩላቸው ዩኒቨርሲቲው ችግር ፈቺ የጥናትና ምርምር ሥራዎች እየሰራ አንደሚገኝ ገልጸው በተለይ የሀገራችን ቱሪዝም ዘርፍ እድገት አስተዋጽኦ የሚያበረክተውን ከኢንስቲትዩቱ ጋር የሚዘጋጀውን የቱሪዝም መዝገበ ቃላት ለማጠናቀቅ ዩኒቨርሲቲው የበኩሉን ያደርጋል ብለዋል።
ይህ የሚሰራው ሥራ እንደ ሀገር ለቱሪዝም ዘርፉ የተሰጠውን ትኩረት፣ የቱሪስቶችን ቆይታ ለማስረዘምና ይረዳል ብለዋል።
የጋራ ስምምነቱን ዓላማ የገለፁት የኢትዮጵያ ቋንቋና ባህል ልማት ኢንስቲትዩት ደይሬክተር ዶ/ር ዮሐንስ መዝገበ ቃላቱ ለሀገራችን ቱሪዝም እድገት አስተዋጽኦ የሚያደርግ መሆኑን ገልጸው በቱሪዝም ማሰልጠኛ ኢንስቲትዩት በኩል ወደ 4000 የሙያ ቃላት መሰብሰቡን ተናግሯል ።
መዝገብ ቃላቱ የሙያ ቃላትም የሚተረገሙበት እና በጉዞና ጉብኝት ፣ በመስተንግዶ እና በመዝናኛ ላይ ያተኮሩ እንደሚሆኑ ገልጸዋል።
Recent Comments