የቱሪዝም ማሰልጠኛ ኢንስቲትዩት ባደረገው ጥናት በሆቴልና የቱሪዝም ዘርፍ የሰለጠነ የሰው ኃይል 47 በቶ ያህሉ ብቻ እንደሆነ የኢንስቲትዩቱ የጥናትና ምርምር ዘርፍ ም/ዋና ዳይሬክተር አቶ ይታሰብ ስዩም ከአዲስ ዘመን ጋዜጣ ጋር ባደረጉት ቃለ ምልልስ ገልጸዋል፡፡

#ጋዜጣ_ፕላስ | በሆቴልና ቱሪዝም ዘርፍ ያለው የሠለጠነ የሰው ኃይል 47 በመቶ ብቻ መሆኑን የቱሪዝም ማሠልጠኛ ኢንስቲትዩት አስታወቀ፡፡የኢንስቲትዩት ምክትል ዋና ዳይሬክተር አቶ ይታሰብ ሥዩም ለአዲስ ዘመን ጋዜጣ እንደገለጹት፤ ኢንስቲትዩቱ በሀገር አቀፍ ደረጃ ባደረገው ጥናት በሆቴልና ቱሪዝም ዘርፍ በቂ የሠለጠነ የሰው ኃይል የለም፡፡ በሀገሪቱ በተለያዩ አካባቢዎች በሚገኙ ባለኮከብ ሆቴሎች፣ ደረጃቸውን በጠበቁ ምግብ ቤቶችና ቱሪስት በሚገለገልባቸው መዳረሻዎች አገልግሎት ከሚሰጡ ባለሙያዎች የሠለጠኑት 47 በመቶ ብቻ እንደሆኑ ተናግረዋል፡፡ቀሪዎቹ 53 በመቶ በልምድ የሚሠሩ መሆናቸውን በጥናት ማረጋገጥ መቻሉንም ነው ያስታወቁት፡፡
ይህ ሁኔታ በአገልግሎት አሰጣጡ ላይ ሰፊ ክፍተት የሚፈጥር መሆኑን ጠቅሰው፤ ለማስተካከል ሥልጠና ላይ ትኩረት ማድረግ ያስፈልጋል ብለዋል፡፡
ያለውን ክፍተት ኢንስቲትዩቱ ብቻ መፍታት አይችልም ያሉት አቶ ይታሰብ፤ የሚመለከታቸው ባለድርሻ አካላት በቅንጀት እንዲሰሩ ጠይቀዋል፡፡
ሆቴሎችም የሀገር ገጽታና አምባሳደሮች በመሆናቸው ከሰው ኃይል ቅጥር ጋር በተያያዘ ከፍተኛ ጥንቃቄ በማድረግ የሰለጠነ የሰው ኃይል መቅጠር እንዳለባቸው አስገዝበዋል፡፡
እንደ አቶ ይታሰብ ገለጻ፤የሆቴል ባለቤቶች የሠለጠነ የሰው ኃይል እንዲቀጥሩ ግንዛቤ መስጠት አስፈላጊ ነው፡፡ ይህም በፍጥነት እየተቀያየረ ከመጣው ዘመንና አዳዲስ ቴክኖሎጂዎችን ለመላመድ ይረዳል፡፡
ፍሬሕይወት አወቀ
+++++++++++++++++
#ጋዜጣ _ፕላስ #Gazetteplus