ቱ. ማ. ኢ ታህሳስ 08/2016 ዓ.ም ቱሪዝም ማሰልጠኛ ኢንስቲትዩት ከሌሎች ዘርፎች ብቻ ሲሰራ የነበረውን ፈጠራ ሥራ ወይም ሀሳቦችን ከቱሪዝምና ከሆቴል ዘርፍ ለማግኘት የሚያስችል ሰልጣኞችን በአንድ ቦታ በማደራጀት ሊሰራ እንደሆነ የቱሪዝም ማሰልጠኛ ኢንስቲትዩት የምርምርና ማማከር ዘርፍ ም/ዋና ዳይሬክተር አቶ ይታሰብ ስዩም ገልጸዋል፡፡
ቱሪዝም ማሰልጠኛ ኢንስቲትዩት ከሌሎች ዘርፎች ብቻ ሲሰራ የነበረውን ፈጠራ ሥራ ወይም ሀሳቦችን ከቱሪዝምና ከሆቴል ዘርፍ ለማግኘት የሚያስችል ሰልጣኞችን በአንድ ቦታ በማደራጀት ሊሰራ እንደሆነ የቱሪዝም ማሰልጠኛ ኢንስቲትዩት የምርምርና ማማከር ዘርፍ ም/ዋና ዳይሬክተር አቶ ይታሰብ ስዩም ገልጸዋል፡፡
ሰልጣኞች ከተቀጣሪነት የሚያወጣ ሥራ መስራት እንደሚቻልና ለሀገር የሚጠቅም ሀሳብ ማፍለቅና እነዚህን ሀሳቦች ሊደግፉ የሚችሉ አሰልጣኞች ስላሉን ጥሩ ሥራዎች እንደሚሰሩ አቶ ይታሰብ ስዩም ተናግረዋል፡፡
ሰልጣኞች ከትምህርታቸው ጎን ለጎን ፈጠራ ሥራዎች ሀሳብ ያላቸው እና ፍላጎት ያላቸው፤ በተሰማሩበት ሙያ የሚታዩ ክፍተቶችን የሚያሟሉ ሥራዎች መስራት እንዳለባቸው በመጠቆም አሁን ለመጀመሪያ ጊዜ በ15 ሰልጣኞች የኢንኩቤሽን ማዕከል ሥራ እንደሚጀምርና ሰልጣኞች በተናጥልና በጋራ ሊሰሩ እንደሚችሉ ተገልጿል፡፡
ሰልጣኞችም በዚህ መሳተፋችን አዳዲስ ሀሳቦችን በሙያችን ማፍለቅ የሚያስችል እድል ይፈጥርልናል ብለዋል፡፡
Recent Comments