ሚያዝያ 8/2014 ዓ ምበሆቴልና ቱሪዝም ዘርፍ በማማከር አገልግሎት አሰጣጥ ላይ ይሰጥ የነበረው የአሰልጣኞች ስልጠና ማጠቃለያ ተደረጓል።

በማጠቃለያው የተገኙት የቱሪዝም ማሰልጠኛ ኢንስቲትዩት ምክትል ዋና ዳይሬክተር አቶ ገዛኸኝ አባተ እንደገለጹት ከዚህ በፊት በኛ ተቋም ይሰጥ የነበረውን የማማከር አገልግሎት ሁሉም በአከባቢው እንዲሰጥና ወጥ ስልጠና እንዲሆን በተፈለገው መሠረት የተሰጠ ነው ።
ህብረተሰቡን ተጠቃሚ ለማድረግ በቅንጅት ከሰራንና ሁላችንም ስራችን ላይ ካተኮርን ማደግ እንደሚቻል በመግለፅ ከዚህ በኋላ በየአካባቢው በስልጠናው መሠረት እንደ አስገዳጅ ተልዕኮ ተቀበሉ በማለት አሳስበዋል።
ተሳታፊዎችም በስልጠናው እንደተጠቀሙና ቀጣይም የአሰልጣኞች ስልጠና እንደመሆኑ ወደተግባር እንደሚገቡ በመግለጽ እንደዚህ አይነት ስልጠናዎች መቀጠል እንዳለባቸው ተናግረዋል።