በሆቴል ሙያ ተመርቀው ወደ ስራ ያልገቡ ባለሙያዎቸ የማነቃቀያ ስልጠና መስጠት ተጀመረ፡፡
ሆ.ቱ.ሥ.ማ.ኢ ግንቦት 02 /2011 ዓ.ም
የባህልና ቱሪዝም ሚኒስቴር እና የሆቴልና ቱሪዝም ሥራ ማሰልጠኛ ኢንስቲትዩት በጋራ በመሆን በተለያየ ጊዜ በሆቴል ዘርፍ ለተመረቁ ስራ ፈላጊዎች የአጭር ግዜ ስልጠና በመስጠት የስራ እድል የሚያገኙበትን ሁኔታ ለማመቻቸት የመጀመሪያ ዙር ስልጠና ተጀመረ፡፡
ተመራቂዎቹ ከሁሉም የሀገራችን ክፍሎች ጥሪ የተደረገላቸው ሲሆን አምስት መቶ ለሚሆኑ ስራ ፈላጊዎች የንድፈ ሀሳብና የተግባር የአጭር ጊዜ ማነቃቀያ ስልጠና ለመስጠት ታቅዶ በአሁኑ ስልጠና 58 የሚሆኑ እየተሳተፉ ይገኛሉ፡፡
ለሰልጣኞች ገለጻ ያደረጉት የኢንስቲትዩቱ ዋና ዳይሬክተር ወ/ሮ አስቴር ዳዊት በሀገራችን የሆቴል ሙያተኞች እጥረት መኖሩን ገልጸው ሰልጣኞቹ የስራ ዕድል የሚያገኙበትን ዕድል ለመፍጠር ከተለያዩ የሆቴል ዘርፍ ማህበራት ጋር እየተሰራ መሆኑን ገልጸዋል፡፡
ስልጣኞቹ የስራ እድል ለማግኘት ዘርፉ የሚፈልገውን የሙያ ስነምግባር በመላበስ ጠንክሮ መስራት እንደሚገባቸው ዋና ዳይሬክተሯ አሳስበዋል፡፡