ግንቦት 8/2011 ዓ.ም በባህልና ቱሪዝም ዘርፍ የሰለጠነ የሰው ሀይል የሚመራበትንና የተቀናጀ አግልግሎት መስጠት የሚቻልበትን መንገድ መፍጠር ታሳቢ ያደረገ የውይይት መድረኩ ላይ በመገኘት መልዕክት ያስተላለፉት የኢፌዲሪ የባህልና ቱሪዝም ሚንስትር ዶ/ር ሂሩት ካሳው እንደገለፁት በየትኛውም መስክ የተሰለፈ አካል ስለሚያከናውነው ተግባር በቂ እውቀት እና ክህሎት ይዞ ወደ ተግባር መግባት ካልተቻለ በዘላቂነት ውጤታማ ሆኖ መቀጠል አዳጋች እንደሚያደርገው ገልፀዋል። አያይዘውም ችግሩን ለመቅረፍ የትብብር ስልጠናዎች የማጠናከርና የማስፋት ጉዳይ በሚመለከታቸው የመንግስትና የግል ተቋማት እንዲሁም በኢንዱስትሪው ባለቤት በኩል ትኩረት ተሰጥቶ ሊሰራ ይገባል ብለዋል።
በመድረኩ ላይ ለዩኒቨርስቲ ኢንዱስትሪ ትስስር መጎልበትና በኢትይጵያ የቱሪዝም እና በሆስፒታሊቲ ኢንዱስትሪ የሰው ሀይል ዳሰሳ በባለሙያዎች ቀርበው ውይይት የሚደረግባቸው ሲሆን በሆቴልና ቱሪዝም ዘርፍ ስልጠና ከሚሰጡ ተቋማትና ባለድርሻ አካላት በጋራ ለመሥራት የሚያስችል ዕቅድ ቀርቦ ውይይት ይደረግበታል።