ሆ.ቱ.ሥ.ማ.ኢ ግንቦት 02 /2011 ዓ.ም በሆቴልና ቱሪዝም ሥራ ማሰልጠኛ ኢንስቲትዩት ተመራማሪዎች በሰሜን ኢትዮጵያና በደቡብ ኦሞ ዞን አካባቢዎች ቱሪዝም ዘርፍ ላይ እየተሰራ ባለው ሁለት ሀገራዊ ጥናት ላይ የመጀመሪያ ዙር ግምገማ ተደረገ፡፡
የምርምርና ማማከር አገልግሎት ክፍል ኃላፊ አቶ ማዘንጊያ ሺመልስ እንዳሉት የምርምር ስራው እንደ ሀገር በዘርፉ የሚታየውን ችግር ለመቅረፍ እንዲቻል ለፖሊሲ ዝግጅት ግብዓት ይሆናል፣ ተቋሙም የተሰጠውን የምርምርና የማማከር ተልዕኮ ለማሳካትና የሚጠበቅበትን እንዲያከናውን አቅጣጫ ለማሳየት ይረዳል ብለዋል፡፡ የተመራማሪዎቹም የተቋሙ መምህራን ይህን መሰል የምርምር ስራ ውስጥ መሳተፋቸው በመስኩ ያላቸውን ልምድ ከማዳበር ባሻገር እንደ ሀገር የዘርፉን ችግር ለመቅረፍ በሚደረገው ጥረት የበኩላቸውን አስተዋጽኦ ያበረክታሉ ብለዋል፡፡
በግምገማ መድረኩ ላይ ከተለያዩ ዩንቨርሲቲዎች፣ ተቋማትና የኢንስቲትዩቱ ተመራማሪዎች ተሳትፎውበታል፡፡
Recent Comments