በሆ.ቱ.ሥ.ማ.ኢ አሰልጣኞችና የምርምርና ማማከር አገልግሎት ዳይሬክቶሬት የሚሰራ ሀገራዊ ጥናት ለማስጀመር የፊርማ ሥነስርዓት ተከናወነ፡፡
ሆ.ቱ.ሥ.ማ.ኢ ታህሳስ 03/2011 ዓ.ም
በሆቴልና ቱሪዝም ሥራ ማሰልጠኛ ኢንስቲትዩት አሰልጣኞችና የምርምርና ማማከር አገልግሎት ዳይሬክቶሬት የሚሰራ የቱሪዝም ዘርፍ ሀገራዊ ጥናት ለማካሄድ ታህሳስ 02/2011 ዓ.ም የፊርማ ሥነስርዓት ተከናወኗል፡፡
የፊርማ ሥነስርዓቱ ላይ የተገኙት የተቋሙ የአካዳሚክና ምርምር ዲን አቶ ግሩም ግርማ ለኢንስቲትዩቱ ከተሰጡት ተልዕኮዎች መካከል በዘርፉ ጥናቶችን በማከናወን ለዘርፉ እድገት አስተዋጽኦ ማድረግ አንዱ መሆኑን ገልጸው ጥናቱ ለሀገራችን የሆስፕታሊቲ ዘርፍ ፖሊሲ ግብዓት ሊሆን ይችላል ብሏል፡፡ አክለውም ለኢንስቲትዩቱ አሰልጣኞችና ተመራማሪዎች መነቃቃትን የሚፈጥርና የተቋሙን የምርምር ስራ ባህልን ለማሳደግ ይረዳልም ብሏል፡፡
የምርምርና ማማከር አገልግሎት ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር አቶ ማዘንጊያ ሺመልስ በበኩላቸው ጥናቱ በቱሪዝም ዘርፍ ሁለት ዋና ዋና ርእሰ ጉዳዮች ላይ የሚያተኩር መሆኑን ገልጸው እስከ ሰኔ 2011 ዓ.ም ድረስ ተጠናቆ ይፋ ይደረጋል ብሏል፡፡
የጥናቱ ቡድን ሰባት አባላትን የያዘ ሲሆን አስፈላጊ ወጪዎችም በተቋሙ እንደሚሸፈን ተገልጿል፡፡