ሆ.ቱ.ሥ.ማ.ኢ ጥቅምት 01/2012 በሆቴልና ቱሪዝም ስራዎች ስልጠና ዙሪያ እየተደረገ ባለው ምክክር በሆቴልና ቱሪዝም ስራ ማሰልጠኛ ኢንስቲትዩት በቀን፣በማታና የአጫጭር ስልጠና መርሐግብሮች ከስድስት ሺህ በላይ ለሚሆኑ ሙያተኞች ስልጠና ለመስጠት እንቅስቃሴ እየተደረገ መሆኑን በውይይት መድረኩ ላይ የ2012 የተቋሙን ዕቅድ ያቀረቡት አቶ ተመስገን በቀለ ገልጸዋል፡፡
በውይይት መድረኩ ኢንስቲትዩቱ ጥራት ያለውን ስልጠና ለመስጠት ርብርብ እየተደረገ መሆኑን ተነግሯል፡፡