በቱሪዝም ማሰልጠኛ ኢንስቲትዩት የገነት ሆቴልን እስከ 45 አመት በማገልገል ጡረታ ለወጡ ሰራተኞች፣ ሆቴሉን በሥራ አስኪያጅነት እንዲያገለግሉ ተመድበው ሲሰሩ የቆዩት አቶ አበበ ኡርጌሳ እንዲሁም በሥራ አመራር ቦርድ አባልነት ያገለገሉትን ግለሰቦች የምስጋናና እውቅና መርሃ ግብር አከናውነናል።

በቦርድ አባልነት የምስክር ወረቀት፣ በጡረታ ለተሰናበቱት የሸማ ውጤቶችና ቦርዱን በሥራ አስኪያጅነት ሲያገለግሉ በመልካም ስነምግባር፣ የሰራተኞችን ችግር በመፍታትና በማበረታታት፣ ከቦርዱ የሚሰጡ ተግባራትን በመቀበል የከርሰምድር ውሃ እንዲወጣ፣ አዳራሽና የሆቴሉን ልዩ ልዩ ክፍሎች እንዲታደስ፣ የመዋቅር ጥናት በማስደረግ አገልግሎቱ እንዲሻሻልና የውጭ ገፅታውን በማሻሻል ላደረጉት ትጋትና ውጤት የወርቅ ሀብል ተበርክቶላቸዋል። ማሰልጠኛ ኢንስቲትዩቱ በርካታ ችግሮች ያሉበት ቢሆንም ከችግሮቹ በላይ እልፍ ምቹ ሁኔታዎች ያሉት በመሆኑ በአዲሱ የመንግስት አደረጃጀት የስልጠና አቅሙ እንዲያድግ፣ በበጀትና በለጋሽ ድርጅቶች ድጋፍ ታግዞ ሰፋፊ የሥራ እድል የሚፈጥሩ የሥልጠና እድሎችን የሚያዘጋጅ በመሆኑ የገነት ሆቴል ከዚህ ቁጥቁጥ እድገት ተላቆ ሞዴል ሆቴል፣ ኢንስቲትዩቱም የልህቀት ማእከል እንዲሆን በሥራና ክህሎት ሚንስትሮቾ ልዩ ትኩረት ተሰጥቶት የተለያዩ እንቅስቃሴዎች እየተደረጉ ነው። ለዚህም የተቋሙ አመራሮችና ማህበረሰብ እንዲሁም ባለድርሻ አካላት በአንድነት በመቆም የተጣለብንን ሃላፊነት እንድንወጣ ጥሪ ለማስተላለፍ እወዳለሁ።