ሆ.ቱ.ሥ.ማ.ኢ ሚያዚያ 25/2011 ዓ.ም የሆቴልና ቱሪዝም ሥራ ማሰልጠኛ ኢንስቲትዩት ከቂርቆስ ክ/ከተማ ሴቶችና ህፃናት ጉዳዮች ጽ/ቤት ጋር በመተባበር በወረዳ 11 ውስጥ የሚገኙ ለችግር ተጋላጭ የሆኑ 50 ሴቶችን ያለባቸውን የኢኮኖሚያዊና ማህበራዊ ችግሮች ለመቅረፍ የሚያስችል የመጀመሪያ ዙር በቤት አያያዝና በምግብ ዝግጅት ለ15 ቀናት የንድፈ ሃሳብና የተግባር ስልጠና ተሰጥቷል፡፡
ስልጠናውን ሲከታተሉ የነበሩ ሰልጣኞችም ከስልጠናው ጥሩ ግንዛቤ ማግኘታቸውን ገልጸው ስልጠና የተከታተሉበት ጊዜ አጭር በመሆኑ ቀጣይነት ሊኖረው እንደሚገባ ጠይቀዋል፡፡
የኢንስቲትዩቱ ዋና ዳይሬክተር ወ/ሮ አስቴር ዳዊት በመጀመሪያ ዙር ስልጠና ላይ የተሳተፉትን ሰልጠኞች ከአዲስ አበባ ሆቴሎች ባለቤቶቸች ማህበር ጋር በመሆን በትብብር ስልጠና ሆቴሎች በመመደብ ተጨማሪ ልምድ እንዲውስዱ ለማድረግ እየተሰራ መሆኑን ገልጸው በሚመደቡበት ቦታ ላይም ለኢንዱስትሪው የሚያስፈልገውን ስነምግባርን በመላበስ የሚሰጡ ስራዎችን በአግባቡ ለመስራት ዝግጅት ማድረግ ያስፈልጋል ብለዋል፡፡
በመጨረሸመ ለስልጠናው መሳካት ጥረት ያደረጉትን ሰራተኞችና መምህራን አመስግነዋል፡፡