ሚያዚያ 11/2011ዓ.ም
የሆቴልና ቱሪዝም ሥራ መሰልጠኛ ኢንስቲትዩት የአካዳሚክና ምርምር ዘርፍ በተቋሙ የትምህርት አሰጣጥና የትምህርት ጥራት ዙሪያ ውይይት ተካሄደ ፡፡
ውይይቱን የተቋሙ አካዳሚክና ምርምር ዲን አቶ ግሩም ግርማ የመሩት ሲሆን የተቋሙ መምህራን በሃገሪቱ ካሉ ሌሎች መምህራን ከቤትና ከሌሎች ከጥቅማጥቅምጋር በተያያዘ ተጠቃሚ አይደለንም የሚልና ሌሎች ተቋማዊ የሆኑ በዘርፉ 50 ዓመታትን እንዳስቆጠረ አንጋፋ ተቋም አሁን ያለንበትን ሁኔታ ምን ላይ ነው የሚል ጥያቄ አንስተው ተወያተዋል፡፡
የተቋሙ ዋና ዳይሬክተር ወ/ሮ አስቴር ዳዊት ከመምህራን ለቀረቡ ጥያቄዎችና አስተያየቶች ምላሽ የሰጡ ሲሆን በተቋም ደረጃ እና በባህልና ቱሪዝም ሚኒስቴር እንዲሁም በቦርድ ሊታዩ የሚገባቸውን ሂደቶች ደረጃ በደረጃ እየፈተሸን ነው፤ በቀጣይም መስተካከል የሚገባቸውን እያስተካከልን እንሄዳለን፤ ለዚህ ደግሞ የናንተ የመምህራን እገዛ ወሳኝ ነው በማለት ተናግረዋል፡፡
በመጨረሻም ተቋሙን በራሳቸው ጥረት የማጣቀሻ ጽሁፍ በማዘጋጀት ከደረጃ አንድ እስከ ሶስት ላሉ ተማሪዎች የሚያገለግል የጣፋጭ ምግብ፤ ዳቦና ኬክ እንዲሁም የአገራችን ባህላዊ ምግብ አዘገጃጀት ሞጁል አዘጋጅተው ያበረከቱትን መምህር ዳንኤል፣ ለተማሪዎች አጋዥ መጽሀፍትን ለቤተመጽሃፍቱ የለገሱትን መምህር ከያ ተስፋዬን እና የቤተመዘክርና ቤተመዛግብት ኤጀንሲን ከተቋሙ ዋና ዳይሬክተር የምስጋና የምስክር ወረቀት ተሰጥቷል፡፡