ቱ.ማ.ኢ መጋቢት 04/2017 ዓ.ም የቱሪዝም ሚኒስቴር እያካሄደ ባለው የዘርፉ ጉባኤ ላይ በኢትዮጵያ የቱሪዝምና ሆስፒታሊቲ መስክ የሰለጠነ የሰው ኃይል ፍላጎትና አቅርቦት ላይ ትኩረት ያደረገ ሀገር አቀፍ ጥናት ቀርቦ ውይይት ተደርጎበታል።
በሆቴልና ቱሪዝም ማሰልጠኛ ኢንስቲትዩት የተጠናው ሰነድ በቱሪዝምና ሆስፒታሊቲ ዘርፍ ውስጥ ከፍቸኛ የሆነ በሰለጠነ የሰው ኃይል ፍላጎትና አቅርቦት ክፍተት እንዳለ ይፋ አድርጓል።
ጥናቱን ያቀረቡት የቱሪዝም ማሰልጠኛ ኢንስቲትዩት የጥናት ምርምርና ማማከር ዘርፍ ምክትል ዋና ዳይሬክተር አቶ ይታሰብ ስዩም እንደገለፁት፤ በዋና ዋና የሀገራችን ከተሞች የተካሄደው ጥናት በመሠረታዊነት በቱሪዝም እና ሆስፒታሊቲ ዘርፍ ያለውን የሰው ሃይል ዝግጁነት፣ አቅርቦት እና የገበያ ፍላጎቶች ላይ ያተኮረ ነው።
የጉባኤው ተሳታፊዎችም በሰነዱ ላይ ጥያቄና አስተያየት አቅርበው ምላሽና ማብራሪያ ተሰጥቶበታል።
የቱሪዝም ሚኒስቴር የመዳረሻ እና መሰረተ ልማት ማስፋፍያ ዘርፍ ሚንስትር ዴኤታ አቶ ስለሽ ግርማ ጥናቱን አስመልክቶ በሰጡት ማብራሪያ ኢትዮጵያን ተወዳዳሪ የቱሪዝም መዳረሻ ለማድረግ ዘርፉ በሰለጠነ የሰው ኃብት እንዲመራ ለማድረግ መሰረታዊ የአስተሳሰብ እና መዋቅራዊ ለውጥ ሊያመጡ የሚችሉ ስራዎችን መሥራት ይገባል።
በባለሙያ ምልመላ ረገድ በኢንዱስትሪው የተሰማሩ ባለድርሻ አካላት እንዲፈጽሟቸው የሚጠበቁ አስገዳጅ መመሪያዎችንም ተግባራዊ ማድረግ እንደሚገባ ከሚኒስቴሩ ያገኘነው መረጃ ያመለክታል፡፡
ትክክለኛ መረጃዎችን ለማግኘት የሚከተሉትን ማስፈንጠሪያዎችን ይጠቀሙ
ፌስቡክ፡ https://www.facebook.com/tticommunication
ቴሌግራም ፡https://t.me/tticommunication
ዌብሳይት፡ https://www.tti.edu.et

Recent Comments