ግንቦት 16/2015 ዓ.ም በቱሪዝም ማሰልጠኛ ኢንስቲትዩትና በገነት ሆቴል ትብብር የቤት ዕድሳት የተደረገላቸው በቂርቆስ ክፍለ ከተማ ወረዳ 11 ነዋሪ ለሆኑ ለወ/ሮ ካሰች አበራ እና ለአቶ መስፍን ገ/እግዚአብሔር የቁልፍ ርክክብ ተደርጓል፡፡

በርክክቡ ወቅት የተገኙት የሥራና ክህሎት ሚኒስቴር ሚኒስትር ዴኤታ ዶ/ር ተሻለ በሬቻ ሥራው ተጠናቆ በማየታቸው ደስታቸውን በመግለጽ፤ ቱሪዝም ማሰልጠኛ ኢንስቲትዩትና ገነት ሆቴል በጋራ በመሆን የሰሩት ሥራ ተጠናክሮ መቀጠል እንዳለበትም ተናግረዋል፡፡
የኢንስቲትዩቱ ዋና ዳይሬክተር አቶ ጌታቸው ነጋሽ በበኩላቸው ይህ ሥራ በሁለት ተቋም ትብብር ብቻ ሳይሆን የወረዳው አመራር አካላት በብዙ እየደገፏቸው እንደተጠናቀቀ በመግለጽ በዚህ ተግባር የተሳተፉትን ሁሉ አመስግነዋል፡፡
ርክክቡ የወረዳው አመራሮች በተገኙበት ተካሂዷል፡፡ የቁልፍ ርክክብ ሲካሄድ በወቅቱ በህክምና ምክንያት ያልተገኙት የአቶ መስፍን ገ/እግዚአብሔርን ቁልፍ የወረዳው ዋና ሥራ አስፈጻሚ ተረክበዋል፡፡